በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ደረሰ

ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ማምሻውን በደረሰን ዜና መሰረት በጎንደር ቀበሌ 18 በሚገኘው  ኢንታሶል   ሆቴል ቦንብ ፈንድቶ ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል።

በሆቴሉ ውስጥ ፋሲል የእግር ኳስ ቡድን የባንክን ቡድን ማሸነፉን ተከትሎ የሚዝናኑ ወጣቶች ነበሩ። ከ5 በላይ በጽኑ የቆሰሉ ሰዎች  ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለማውቅ የተቻለ ሲሆን፣ ወታደሮችና ፖሊሶች አካባቢውን በመክበባቸው በትክክል የሞቱና የቆሰሉ ሰዎችን ቁጥር ለማወቅ አልተቻለም።

ዛሬ ማክሰኞ ጥር 2 ቀን 2009 ዓም ጠዋት ላይ ደግሞ አቶ ባረኮ በሚባል ቦታ ላይ ማንነታቸው አልተወቁ ሃይሎች አንድ የፌደራል ገድለው የጦር መሳሪያውን ይዘው ተሰውረዋል።  ትናንት ዋርካ በሚባለው አካባቢም እንዲሁ መጠነኛ የቦንብ ፍንዳታ ተከስቶ ነበር።

ፍንዳታውን ማን እንዳደረሰው የታወቀ ነገር የለም። በቅርቡ በባህርዳር ከተማ በአንድ ሆቴል ላይ ተመሳሳይ ፍንዳታ መድረሱ ይታወቃል።