በግብጽ 37 ግለሰቦች ላይ የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 5/2010) የግብጽ ፍርድ ቤት በሰው አካል ንግድ ላይ ተሰማርተው ተገኝተዋል ባላቸው 37 ግለሰቦች ላይ የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተሰማ።

በሃገሪቱ የሚታተም አንድ ጋዜጣ ለንባብ እንዳበቃው የካይሮ ፍርድ ቤት በወንጀሉ ተሳትፈዋል ባላቸው ግለሰቦች ላይ ከ 7- 15 አመት ቅጣት ማስተላለፉን አስነብቧል።

ከተከሳሾቹ መካከል በህገወጥ የአካል ዝውውሩ ላይ የጤና ባለሙያዎችም እንደሚገኙበት ታውቋል።

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ግብጻውያን በህገወጥ መንገድ አካላቸውን በመሸጥ ገንዘብ እንደሚያገኙም ጋዜጣው አስነብቧል።