በዱራሜ ስራ እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን በፖሊሶች ተደበደቡ

በዱራሜ ስራ እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን በፖሊሶች ተደበደቡ
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ/ም ) በከምባታ ጠምባሮ ዞን ካለፉት 4 ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው ስራ ያጡ ወጣቶች ወደ ዞን መስተዳደር ምክር ቤት ማምራታቸውን ተከትሎ በፖሊሶች ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።
ተማሪዎቹ ቀደም ብለው ጥያቄያቸውን ለመስተዳድሩ አቅርበው ለዛሬ አርብ ተቀጥረው የነበረ ቢሆንም፣ በቀጠሮአቸው መሰረት ወደ መስተዳድሩ ሲሄዱ ያጋጣማቸው የፖሊስ ዱላ ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ የከተማውን የአስተዳደር አካላት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።