በዛሬው ዕለት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ የነበሩ የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች የመኪና አደጋ እንዳጋጠማቸው ተዘገበ።

በዛሬው ዕለት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ የነበሩ የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች የመኪና አደጋ እንዳጋጠማቸው ተዘገበ።
( ኢሳት ዜና መስከረም 29 ቀን 2011 ዓ/ም ) ቢቢሲ እና አንዳንድ መገናኛ ብዙሀን የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮን ዋቢ አድርገው እንደዘገቡት ፣የትህዴን አባላት ኤርትራ ከሚገኘው ቤዛቸው ተነስተው ወደ ዛላምበሳ እየተጓዙ ሳለ ሰገንቲ አካባቢ ሲደርሱ ነው አደጋው ያጋጠማቸው።
በአደጋው የተወሰኑ ወታደሮች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተመልክቷል።
ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት ዛሬ ማለዳ ከኤርትራ የተነሱ ወደ 2000 የሚጠጉ የትህዴን ወታደሮች- የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ ዛላምበሳ ገብተዋል።
በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ ከቆዩ የኢትዮጵያ ድርጅቶች መካከል አንዱ የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያ ንቅናቄ መሆኑ ይታወቃል።
እንደ አብዛኞቹ የትጥቅ ድርጅቶች ውስጥ መሰረቱን በኤርትራ አድርጎ ሲንቀሳቀስ የቆየው ትህዴን፣በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ሰላም መፈጠሩን ተከትሎ ከኢትዮጵያ መንግስት የቀረበውን የሰላም ጥሪ እንደሚቀበለው ማስታወቁ ይታወሳል።