በከፋ ዞን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ከ15 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ

በከፋ ዞን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ከ15 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ
( ኢሳት ዜና መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ/ም )የአካባቢው ባለስልጣናት ለኢሳት እንደተናገሩት ባለፉት 3 ቀናት ማንነታቸው የማይታወቁ ታጣቂዎች በከምባታ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ ነው።
የቡልካቡል ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ታደለ ለኢሳት በስልክ እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ቀናት ከ15 ያላነሱ ሰዎች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተገድለዋል። ይህንን ጥቃት ተከትሎ በርካታ ዜጎች አካባቢያቸውን ለቀው ሸሽተዋል። ችግሩ ላለፉት 2 ዓመታት የቆዬ ቢሆንም፣ ሰሞኑን ጥቃቱ መጨመሩን ሊመቀንበሩ ተናግረዋል
የታጣቂዎችን ማንነት እንደማያውቁ የገለጹት ሊቀመንበሩ ፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው። ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚፈናቀሉ የኦሮሞ፣ የአማራና የሌሎች ብሄር ተወላጆች ወደ ኦሮምያ ክልል በመግባት ላይ ሲሆኑ፣ የክልሉ መንግስት ተፈናቃዮችን ለመርዳት ጥረት እያደረገ ነው። መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው የገባ ቢሆንም፣ ዜጎች ግን ጥቃቶችን በመፍራት አካባቢውን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው።