በኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የሚያስተባብር ልዩ ቢሮ በዋሽንግተን ዲሲ ሊቋቋም ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 5/2011) አዲስ አበባ ውስጥ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የሚያስተባብር ልዩ ቢሮ በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚቋቋም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ  ገለጹ።

ኢንጅነር ታከለ ኡማ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በኢትዮጵያ ኢምባሲ ተገኝተው ባሰተላለፉት መልዕክት ሁሉም ባለው እዉቀት እና ልምዱን በማስተባበር አዲስ አበባን እንዲለውጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሰደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው ከኢትጵያዊያኑ ጋር ትውውቅ በማድረግ ከሁሉም ጋር በቅርብ በመስራት ኢምባሲው ለኢትዮጵያዊኑ ተደረሽ አገልግሎት እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መዲና ከተማችሁን በጋራ አልሙ ሲሉ ጥሪ አቀርበዋል።

ዋና ከተማችሁ አዲስ አበባ ሃገራችሁ ደግሞ ኢትዮጵያ ናት ሲሉም ሁሉም በጋራ እንዲቆሙ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ጥሪ አቅርበዋል።

እናም አሉ ኢንጂነር ታከለ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአንድነት መንፈስ ሃገራችንን ለመለወጥ ልንረባረብ ይገባል ነው ያሉት።

በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሰደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው ከኢትጵያዊያኑ ጋር ትውውቅ በማድረግ ከሁሉም ጋር በቅርብ በመስራት ኤምባሲው ለኢትዮጵያዊኑ ተደራሽ አገልግሎት እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት ስነስርአት የህብረት ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ታየ ዲበኩሉ እና ሌሎችም አመራሮች ተገኝተው  ለዲያስፖራው የኢንቨስትመንት ፍላጎት ባንኩ ብድር ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

የሕብረት ባንክ ተቀማጭ ካፒታል ሁለት ቢሊየን ብር ሲሆን የአክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ወደ 5 ቢሊየን እንዲያድግ በመወሰኑ ወደፊት የአክሲዮ ሽያጭ እንደሚጀምርም የባንኩ ፕሬዝዳንት አስታውቀዋል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ታየ ዲበኩሉ እንደገለጹት ተቋማቸው በውጭ ምንዛሪ አካውንት ለሚከፍቱና ወደ ብር ተቀይሮ በቁጠባ ሂሳብ ለሚያስቀምጡ ዲያስፖራዎች በሀገሪቱ ገንዘብ እስከ 14 በመቶ ወለድ ይከፍላል።

እስከ 20 በመቶ መነሻ ካፒታል ላለቸው ደግሞ ባንኩ እስከ 80 በመቶ ብድር እንደሚያመቻችም  ገልጸዋል።