በአጣዬና ማጀቴ የተፈጠረውን ችግር መቆጣጠሩ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 30/2011)በሰሜን ሸዋ አጣዬና ማጀቴ የተፈጠረውን ችግር መቆጣጠሩን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ።

የክልሉ ጸጥታና ሰላም ቢሮ ምክትል ሃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ የሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች ያለውን አለመረጋጋት በመቆጣጠር ሰላም እንዲሰፍን ተደርጓል።

በዛሬው ዕለት የክልል የተለያዩ የጸጥታ ሃይሎች አካባቢዎችን የማረጋጋት ስራ እያከናወኑ መሆኑን የጠቀሱት ኮሎኔል አለበል አማረ ጥቃት የፈጸሙት ሃይሎች ወደ መጡበት አካባቢ መመለሳቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ሃይሎች የኦነግ ታጣቂዎች መሆናቸውን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላቸው ምክትል ሃላፊው በምርመራ ላይ በመሆናችን በቅርቡ ውጤቱን እናሳውቃለን ብለዋል።