በአጣዬና ማጀቴ አካባቢ በተከሰተው የጸጥታ ችግር 27 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 2/2011)በሰሜን ሸዋ አጣዬና ማጀቴ አካባቢ በተከሰተው የጸጥታ ችግር 27 ሰዎች መገደላቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቁ።

ፋይል

ከተገደሉት መካከል ሦስቱ የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት መሆናቸው ታውቋል።

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ተፈራ ወንድማገኘሁ ለመንግታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ የተከሰተው የጸጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።

አቶ ተፈራ ችግሩ የአማራ የኦሮሞ ህዝብ አጀንዳ አይደለም ሲሉም ገልጸዋል።

ከተገደሉት በተጨማሪ ከ20 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት መደረሱን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።