በአዋሳ ትልቁ የገበያ ማዕከል በደረሰ ቃጠሎ ከፍተኛ ንብረት ወደመ

በአዋሳ ትልቁ የገበያ ማዕከል በደረሰ ቃጠሎ ከፍተኛ ንብረት ወደመ
( ኢሳት ዜና መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ/ም ) ቃጠሎው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ተነስቶ እስከ ጠዋት ድረስ መቀጠሉንና በዚህም የተነሳ በርካታ የንግድ ድርጅቶች ወድመዋል። የቃጠሎውን ምክንያት ለማወቅ ባይቻልም፣ አንዳንድ ነዋሪዎች ግን ቃጠሎው ሆን ተብሎ እንደተነሳ ይገልጻሉ። ውሃ ሳይዝ ወደ በአካባቢው የተገኘ የከተማው እሳት አደጋ መኪና በህዝቡ በድንጋይ ተሰባብሯል።ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርም በፖሊስ እንዲበተን ተደርጓል።