በአንድ የልዩ ጥበቃ ፖሊስ አዛዥ ቤት 500 የሚሆኑ ሽጉጦች ተገኙ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2011)በባህርዳር ከተማ በአንድ የልዩ ጥበቃ ፖሊስ አዛዥ ቤት ውስጥ 500 የሚሆኑ ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ልዩ የጥበቃ ሃላፊ የሆኑት ኮማንደር ውበቱ ሽፈራው ከመኖሪያ ቤታቸው 498 ሽጉጦች መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ታህሳስ 22/2011 ሰኞ ምሽት በመኖሪያ ቤታቸው 498 ሽጉጦችን ደብቀው የተገኙት የፖሊስ ሃላፊ የጦር መሳሪያውን ለምን እንዳከማቹና ከየት እንደሰበሰቡት የተገለጸ ነገር የለም።

ፖሊስን ጠቅሶ የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው ኮማንደሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በሌሎችም ላይ ፖሊስ ምርመራ መቀጠሉን የባህርዳር ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ ምክትል ኮማንደር አየልኝ ተከልሎ ገልጸዋል።