በአርባምንጭ ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ ተካሄደ

በአርባምንጭ ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ ተካሄደ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከንጋቱ 11 ሰዓት ላይ የአርሶአደሮችን ቤት ለማፍረስ በአጋዚ፣ በልዩ ሃይል እና በአካባቢው ፖሊሶች ታጅቦ የተገኘው አፍራሽ ግብረሃይል ተቃውሞ አጋጥሞታል። አርሶአደሮች ከቀያችን የምታፈናቅሉን እኛን ገድላችሁ ነው የሚል አቋም በመያዛቸው ፣ ወታደሮች በህዝቡ ላይ የጭስ ቦንብ በመወርወርና ተኩስ በመክፈት ለመበተን ሞክረዋል። ህዝቡ ሲሸሽ እንደገና ቤት ለማፍረስ ሲሄዱ ህዝቡ ተመልሶ በድጋሜ ተቃውሞውን ገልጿል።