በአላማጣ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ አይከፈላችሁም ተባሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በአላማጣ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የምከፍለው ደሞዝ የለኝም ሲል የትግራይ ክልላዊ መንግስት ማሳሰቢያ ሰጠ።

የፌደራል መንግስቱ ተጨማሪ በጀት እንዲሰጠን ስለጠየቅን እስከዛው ድረስ የምከፍለሰ በጀት የለኝም ሲሉ የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

ተወላጆቹ የክልሉ መንግስት እየወሰደ ያለው ርምጃ አግባብነት የሌለውና እኛን ለማጥቃት ሆን ብሎ ያቀደው ነው ሲሉ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።