በብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና በግብረ አበሮቻቸው ላይ ክስ ተመሰረተ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2011) በብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና በግብረአበርነት በተያዙት የሜቴክ የስራ ሃላፊዎች ላይ ዛሬ በይፋ ክስ መመስረቱ ተሰማ።

በተለያዩ ሰባት የሙስና ወንጀሎች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁንዲ፣ረመዳን ሙሳ፣ኮለኔል ደሴ ዘለቀ፣ቸርነት ዳናን ጨምሮ 8 ሰዎች መሆናቸው ተመልክቷል።