በባንግላዴሽ 140 ኪሎ ግራም የሚመዝን የኢትዮጵያ ጫት ተያዘ

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 5/2010) በባንግላዴሽ ዳካ አውሮፕላን ማረፊያ 140 ኪሎ ግራም የሚመዝን የኢትዮጵያ ጫት በቁጥጥር ስር ዋለ።

ዴይሊ ስታር ከዳካ እንደዘገበው የባንግላዴሽ የጉምሩክና የጸጥታ ሰራተኞች በትብብር ትላንት በቁጥጥር ስር ያዋሉት 140 ኪሎግራም የኢትዮጵያ ጫት ከህንድ ወደ ባንግላዴሽ መጓዙም ተመልክቷል።

ዴይሊ ስታር የኢትዮጵያ ማሪዋና በሚል የገለጸው ጫት ለምርመራ መላኩም ተመልክቷል።

ጫቱ ከኢትዮጵያ ወደ ህንድ እንዴት እንደሔደ የተገለጸ ነገር የለም።

ከጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ 31 ላይ 460 ኪሎ ግራም ጫት በተመሳሳይ ሲያዝ መስከረም 8 ላይ ደግሞ 160 ኪሎግራም ጫት ባንግላዴሽ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተመልክቷል።