በቀይ ሽብር ጊዜ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸመ ኢትዮጵያዊ ጥፋተኛ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 18/2011) በኢትዮጵያ በቀይ ሽብር ጊዜ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸመ ኢትዮጵያዊ በተጭበረበረ መንገድ የአሜሪካ ዜግነት በማግኘቱ በቨርጂኒያ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባለ።

መርጊያ ንጉሴ ሃብተየስ የተባለውና የ58 ዓመት ዕድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ የሃገሪቱን ህግ በመጻረር በኢትዮጵያ በቀይ ሽብር ጊዜ መሳተፉን ሳይገልጽ በሃሰት መረጃ የአሜሪካን ዜግነት አግኝቷል።

ግልሰቡ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ ጥፋተኝነቱን በማመኑም ለመጭው ግንቦት የመጨረሻውን ፍርድ ሊያገኝ ቀጠሮ መያዙን ጀስቲስ ኒውስ ዘግቧል።