በሻሸመኔ አንድን ግለሰብን ዘቅዝቀው የሰቀሉ ለፍርድ ቀረቡ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) በሻሸመኔ ከተማ ባለፈው ነሐሴ አንድን ግለሰብ ዘቅዝቀው በመስቀል የገደሉና በዕለቱ ብጥብጥ አስነስተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ለፍርድ መቅረባቸው ተገለጸ።

ነሐሴ 6 ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን ቡድን በተዘጋጀው አቀባበል ላይ ግርግርና ሁከት በመፍጠር ግለሰቡን በአሰቃቂ ሁኔታ ግድለዋል ተብለው ከተጠረጠሩት 14 ግለሰቦች 6ቱ በትላንትናው ዕለት በምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ለማወቅ ተችሏል።

የሻሸመኔውን ሁከት ተከትሎ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ በሌሎች አካባቢዎች ያቀዳቸው ተመሳሳይ ፕሮግራሞች መሰረዛቸው የሚታወስ ነው።