በሶማሌ ክልል ለመፍጠር ታስቦ የነበረው የሽብር ጥቃት ከሸፈ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 26/2011) የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት በክልሉ ሽብር ለመፍጠር ያደረጉት ሙከራ ከሸፈ።

በዚህ የሽብር ጥቃት ሙከራ ኢላማ የተደረጉት የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ፣ መብራት ሃይል፣ ኢምግሬሽን፣ ባንኮችና ህዝብ የሚበዛባቸው አካባቢዎች እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል።

የክልሉ የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ አብዲ አቢ ለኢሳት እንደገለጹት የተሸረበው የሽብር ጥቃት በቀድሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት በአቶ አብዲ ኢሌ በተሰጠ ትዕዛዝ በአጎታቸው አማካኝነት የሚፈጸም እንደነበር እና አጎታቸው እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል።