በሱዳን ጭንብል ያጠለቁ የጸጥታ ሃይሎች ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን ሲያሰቃዩ የሚያሳይ ምስል ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2011) በሱዳን ጭንብል ያጠለቁ የጸጥታ ሃይሎች አልበሽር ከስልጣን ይውረዱ በሚል ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞችን ሲያባርሩ፣ሲደበድቡና ወደ ሚስጥራዊ የማሰሪያ ስፍራ እየጎተቱ ሲወስዱ ያሚያሳይ ምስል ይፋ ሆነ።

ቢቢሲ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ ድርጊቱን የሚፈጽሙት የጸጥታ ሃይሎች ድርጊቱን የሚፈጽሙት ታርጋ በሌላቸው ተሽከርካሪዎች ነው።

እንደ መረጃው ከሆነ ሰልፈኞቹን ለመያዝና ወደ ሚስጥራዊ የማሰሪያ ስፍራዎች ለመውሰድ ሚስጥራዊ የደህንነት ሰዎች ተመድበዋል።

በሱዳን ወራትን ባስቆጠረው ተቃውሞ በሰልፈኞቹ ላይ የተፈጸሙ አሰቃቂ ድርጎቶችን የሚያሳዩ በምስል የተደገፉ ማስረጃዎች በእጁ እንዳሉም ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል።

ከአሰቃቂ እስር ቤት የተረፉ ዜጎችም የእስር ቤቱን ስፋትና አሰቃቂነት ብሎም እንደ ፍሪጅ የሚቀዘቅዘውን የእስር ቤቱን ገጽታ ለቢቢሲ እማኝነታቸውን ሰተዋል።