በሰሜን ሸዋና የኦሮሞ አስተዳደር ዞን የጦር መሳሪያ ዝውውር ገደብ ተጣለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011) በኮማንድ ፓስት ስር በሚገኙት የሰሜን ሸዋና የኦሮሞ አስተዳደር ዞን የጦር መሳሪያ ዝውውር ገደብ መጣሉ ተገለጸ።

ሕገ ወጥ የጦር የመሣሪያ ዝውውር በቅርቡ ለተከሰቱት የፀጥታ ችግሮች መንስኤ ናቸው ያለው ኮማንድ ፖስት  ከፌደራልና ከክልል ጸጥታ ሃይሎች ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ በተገኘ ማንኛውም አካል ላይ ርምጃ እንደሚወሰድበት አስታውቋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአካባቢዎቹ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ዝውውር ይደረግ እንደነበረ የጠቀሱት የጸጥታ አካላት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተቋቋመው  የፀጥታ ጥምር ኃይል ለህገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ነው።