በማእከላዊ ዜጎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው

ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት ሸራተን እየተባለ በሚጠራው የእስር ቤቱ ክፍል የሚገኝ ዘርኣይ አዝመራው የሚባል ከደባርቅ አካባቢ የመጣ ወጣት አባትህ ሸፍቷል በሚል በአሌክትሪክ “ ሾክ” ስለተደረገ ሰውነቱ እንደሚንቀጠቅ፣ በራሱ መሄድ ባለመቻሉም በድጋፍ እንደሚጓዝ ታውቋል።
ሌሎችም በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች ተይዘው የመጡ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ ድብደባ የተፈጸመባቸው በመሆኑ ለአካል ጉዳት ተደርገዋል። አእምሮን በሚጎዳ የዘረኝነት ስድብ እየተሰደቡ ከፍተኛ ስቃይ እንደደረሰባቸው ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንዲደርሱላቸው በእስር ቤቱ ውስጥ ያሉ ዜጎች ጥያቄ አቅርበዋል።