በለንደን ግሪንፊልድ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ 5 ኢትዮጵያውያን ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2009)

በእንግሊዝ ለንደን ግሪንፊልድ ህንጻ ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ኢትዮጵያውያን ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነገረ። 

በ28ኛው ፎቅ ላይ የነበሩት አባት፣ እናትና 3 ልጆቻቸው በቃጠሎው ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተፈርቷል። ልጆቹ የ5፣ የ12 እና የ14 አመት ዕድሜ ያላቸው መሆናቸው ታውቋል።

በለንደኑ ቃጠሎ እስካሁን የ17ቱ ሰዎች ሞት ሲረጋገጥ 18ቱ ደግሞ በሞትና በህይወት መካከል ክፉኛ ቆስለው እንደሚገኙ ተነግሯል። የአፍሪካ ስደተኞች በብዛት ይኖሩበታል በተባለው በዚሁ ህንጻ ከ34 በላይ የሚሆኑት ሰዎች የደረሱበት አለመታውቁ እየተነገረ ነው።