በሃረር ለረጅም ጊዜ ሲያገለግል የነበረው ቄራ ተዘጋ

በሃረር ለረጅም ጊዜ ሲያገለግል የነበረው ቄራ ተዘጋ
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ/ም ) በከተማው ቀበሌ 8 የሚገኘው ቄራ በመዘጋቱ እርድ መቆሙን የከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል። አንዳንድ ነዋሪዎች ቄሮዎች እንዳዘጉት የገለጹ ሲሆን፣ የቀበሌ 8 የቄሮ ተወካይ ወጣት ሚስባህ ግን ቄሮ ቄራው እንዲዘጋ አለመስደረጉንና የወረዳው መዘጋጃ ከጤና ጋር በተያያዘ መዝጋቱን ገልጿል።
የሸንኮር ወረዳ አስተዳደሪ አቶ አብዱረህማን አሰፋም እንዲሁ ቄራው የተዘጋው ከንጽህና ጋር በተያያዘ የጤና ባለሙያዎች ከገመገሙ በሁዋላ መሆኑን ገልጸዋል።