ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች የርሃብ አድማ አደረጉ

ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች የርሃብ አድማ አደረጉ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) የረሃብ አድማው “ግንቦት 20 ለባርነት የተዳረግንበት ቀን ነው፣ እየተሰቃየን ያለነው በግንቦት 20 ቀን ወደ ስልጣን በወጡት ነው” በሚል ምክንያት መሆኑን ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል። እስረኞቹ ከቂሊንጦ እስር ቤት የሚሰጣቸውን ምግብ “አንቀበልም” በማለት መልሰዋል።
በአሁን ሰዓት ከ250 በላይ የክስ ሂደታቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ቂሊንጦ ውስጥ ይገኛሉ። የ”ሽብር” ክስ ከተመሰረተባቸው እስረኞች መካከል አብዛኛዎቹ በማዕከላዊ እና በቂሊንጦ እስር ቤት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል።