ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ ከሃላፊነታቸው ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 2/2011) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገለጸ።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሹመቱ የተሰጣቸው ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ ከሃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያት በጡረታ እንደሆነ በተሰጣቸው ደብዳቤ ላይ መገለጹን ሪፖርተር ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኮሚሽነሩ በጡረታ እንዲገለሉ ማድረጋቸውን ከመገለጹ ውጪ ዝርዝር ምክንያት አልተሰጠም።

በሌላ በኩል የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሃላፊ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

አቶ ኑሪ ሁሴን ከወራት በፊት ከአዋሽ ባንክ ተዛውረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት የሆኑት የአቶ ባጫ ጊና ምክትል ሆነው እንደተሾሙ ተገልጿል።