ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አዲስ የቦርድ አባላት ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 12/2011) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አዲስ የቦርድ አባላትን ሹመት አፀደቀ።

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት አዲስ የቀረቡ ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባላትን ሹመት በዛሬው ዕለት መደበኛ ስብሰባው ላይ አፅድቋል።

በዚሁ መሰረት አቶ ፍቃዱ ተሰማ ሰብሳቢ  ሆነው ሲሾሙ አቶ ተፈራ ደርበዉ ፥ ዶ /ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አባል ፥ ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ፥ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ እና ዶ /ር አብዲዋስ አብዱላሂ  አባል ሆነው ተሹመዋል።

የኮርፖሬሽኑ ነባር የቦርድ አባላት የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ወ/ሮ ካሚላ ጁንዲ አባልነታቸው እንደተጠበቀ እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥንን የሚመራው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስራ አስኪያጆች እና መምሪያ አባላት ግን አሁንም በኢህአዴግ ካድሬዎች እንደሚመራ ይነገራል።

ሰራተኞችም አሁምን የሚዲያ ነጻነት በሌለበት ሁኔታ እንደሚሰሩ የውስጥ ምንጮች ይገልጻሉ።