ለኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ለ10 ቀናት ተራዘመ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የተሰጠ መግለጫ፣

መጋቢት 11 ቀን 2003 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ሥራ ከጀመረ ካለፈው የሚያዚያ ወር 2002 ዓም ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች ያጋጠሙትን ችግር
እየተቋቋመ በርካታ ፕሮግራሞችን በቀጥታ ወደ ሀገር ቤት በማስተላለፍ ከፍተኛ የህዝብ ቀልብ ለመሳብ በቅቷል፣ ይህን ሥራውን ዛሬም
ቀጥሏል።
ኢሳት አሁን ባለበት ደረጃ ወደ ሀገር ቤት የሚሰጠውን አግልግሎት እንዲቀጥልና በውጭ ሀገርም የቴሌቪዥን አገልግሎት ስርጭት
ለመጀመር ያለውን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ከዚህ በፊት ከነበረው በላይ ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ የማሰባሰብ ወሳኝ ደረጃ ላይ
በመድረሱ፣ ከጃንዋሪ 15 2011 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ወራት የሚቆይ የ 1 (አንድ) ሚሊዮን ዶላር የማሰባሰብ ዘመቻ መጀመሩ ይታወሳል።
ባለፉት ሁለት ወራት በአለም ዙርያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ኢሳትን ለመርዳት ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። በገንዘብ የተሰበሰበው
በጣም ውስን ቢሆንም እስካሁን ድረስ፣ አብዛኛው ተቆርቋሪ የመግዛት ፕሌጅ (PLEADGE) በማድረጉ፣ እንዲሁም የማርችን ደሞዝ
እንዲጠቀሙ የዘመቻው የመጨረሻው ማለቂያን ቀን ለ10 ቀናት እንዲራዘም በስፋት በመጠየቁ፣ የመጨረሻው ቀን እስከ ማርች 31፣ 2011
ተራዝሟል።
ይህ የገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለኢሳት የሚረዳው ገንዘብ እውነተኛ መረጃ ሊያመጣ የሚችለውን ከፍተኛ የነፃነት
ተስፋ በአስተማማኝ መሰረት ላይ የሚያቆም በመሆኑ፣ ለዚህ ዓይነት ታሪካዊ ለውጥ በሚያደርጉት የገንዘብ ዕርዳታ ኢትዮጵያንና ህዝቧን
በመታደግ ሊኮሩበት ይገባል እንላለን። ዛሬ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ተገድቦ የለውጥ ማነቆ በሆነበት ሁኔታ የኢሳትን ፕሮግራሞች
በመላው ኢትዮጵያና የአለም ክፍሎች ለሚገኙ ወገኖቻችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማዳረስ ከምናደረገው ጥረት የበለጠ ሀገር እና ወገንን
የሚታደጉበት ጥረት ስለሌለ የሚቻልዎትን ዕርዳታ እንዲያደርጉል እንጠይቃለን።
ሰሞኑን የአምባገነኑና አፋኙ ስርአት ኢሳትን ከአየር ለማስወገድ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ተቋቁመን፣ አሁን ባለንበትም ሆነ በሌሎች
ሳተላይቶችና ሞገዶች ስርጭታችንን ለመቀጠል የገንዘብ ጉዳይ ወሳኝ በመሆኑ የዘመቻውን ትኬት በመግዛት የራሶን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ
ወገናዊ ጥሪያችንን አሁንም በድጋሚ እናቀርባለን።
ኢሳትን መደገፍ ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የምትገኘውን ሀገራችንና ወገናችንን መታደግ ነው።
የኢሳት የነጻነት መንፈስ ለዘላላም ይኑር!!! ኢሳት የኢትዮጵያዊያን ልሳን ነው!!!
ኢሳት፣
www.ethsat.com