ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ አዲስ ስራ አስኪያጅ ተሾመ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011) ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ምትክ አዲስ ስራ አስኪያጅ ተሾመ።

የኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ለግድቡ ግንባታ በዋና ስራ አስኪያጅነት የሾሙት ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮን መሆኑ ታውቋል።

ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳንና አቶ ፍቃዱ ከበደ ደግሞ በምክትል ስራ አስኪያጅነት መሾማቸውም ይፋ ሆኗል።

አዲሶቹ ተሿሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ስራቸውን እንደሚቀጥሉም ታውቋል።

በምክትል ስራ አስኪያጅነት የተሾሙት ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን ከኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት በኋላ በተጠባባቂ ስራ አስኪያጅነት ሲሰሩ መቆየታቸውንም ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገባ መረዳት ተችሏል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሐምሌ 19 ቀን 2010 አምተምህረት አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ይታወሳል።

ፖሊስ አደረኩት ባለው ምርመራ ኢንጂነሩ ስመኘው ራሳቸውን እንዳጠፉ መግለጫ መስጠቱም አይዘነጋም።