ህወሃት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ለመቃወም በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እያዘጋጀ ነው

ህወሃት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ለመቃወም በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እያዘጋጀ ነው
(ኢሳት ዜና ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት እየተወሰዳቸው ያሉትን የለውጥ እርምጃዎች የሚቃወሙ የተቃውሞ ሰልፎች ለመጪው እሁድ እየተዘጋጁ ነው።
ሰልፉን እኛን አይመለከተንም እያሉ ያሉ የራያ ተወላጆች ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው። የራያ ወጣቶች የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ይዘው ከተገኙ ወይም ዶ/ር አብይ አህመድን ምስል የያዘውን ቲሸርት ለብሰው የተገኙ በርካታ ወጣቶች ታስረዋል።
የራያ ህዝብ በእሁዱ ሰልፍ ላይ እንዲገኝ ፊርማ እንዲያስቀምጥ እየታዘዘ ነው። በአካባቢው የሚታየው ውጥረትም ጨምሯል። በጉዳዩ ዙሪያ በራያ የማንነት ጉዳይና በሰብአዊ መብቶች መከበር ዙሪያ ትግል የሚያደርጉትን አቶ አግዘው ህዳሩን አነጋግረናቸዋል።
አቶ አግዘው ህዝቡ ፍትህን የሚፈልግ፣ እኩልነትን የሚፈልግ፣ የሚናፍቀውን ኢትዮጵያዊነቱን የሚናፍቀው የራያ ህዝብ በጨቋኞችና ሴረኞች ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይሳተፉ መልዕክት አስተላልፈዋል።