ሃረር ከተማ በቆሻሻ የተነሳ ወረርሽኝ ያሰጋታል ተባለ

ሃረር ከተማ በቆሻሻ የተነሳ ወረርሽኝ ያሰጋታል ተባለ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ/ም ) በሃብሊና በኦህዴድ መካከል ያለውን አለመግባባት ተከትሎ የከተማው ቆሻሻ ይደፋበት የነበረው በከር የሚባለው አካባቢ ላይ ቄሮዎች ቆሻሻ እንደማይደፋ በመከልከላቸው ምክንያት በከተማው ያለው ቆሻሻ መብዛት ለበሽታ እየዳረጋቸው ነው። ወኪላችን እንደገለጸው መንግስት ቆሻሻውን ወስዶ መድፋት ባለመቻሉ ቆሻሻው ከተማ ውስጥ እንዲከበር ሆኗል።
በተለይ ትልቁ የገበያ ማእከል በሆነው ሸዋበር አካባቢ ከፍተኛ የቆሻሻ ክምር እንደሚታይና በአካባቢው ለስራ የሚሄዱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ምሬታቸውን እየገለጹ ነው።