ለ18 ዓመታት በስራ ላይ የቆየው ሕግ ሕገመንግስትን ይጥሳል ተባለ

ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴሬሽን ምክርቤት ላለፉት 18 ዓመታት በስራ ላይ የነበረውና የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔን ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት ጉዳያቸው የታየበት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8  ተራ ቁጥር 1 እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7 ተራቁጥር 1 ሕገመንግስቱን እንደሚጥሱ በመወሰን የመላኩ ፈንታን አቤቱታ ውድቅ ...

Read More »

በስደት ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሩዋንዳው የደህንነት አዛዥ ተገደሉ

ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ በስደት ላይ የሚገኙት የሩዋንዳ የደህንነት ዋና አዛዥ የነበሩት ፓትሪክ ካሪጋያ የተገደሉት ጆሀንስበርግ  በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ነው። የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እንዳለው የሩዋንዳ መንግስት ተቃዋሚ የሆኑት ካሪጋያ የተገደሉት በገመድ ታንቀው ሳይሆን አይቀርም። የ53 አመቱ ሚ/ር ካሪጋያ ላለፉት 6 አመታት  በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በስደተኝነት ቆይተዋል። ኮሎኔል ካሪጋያ ከፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ከተጋጩ በሁዋላ ...

Read More »

በደቡብ ክልል የይርጋ ጨፌ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መምህራኑ አድማውን የጀመሩት ያለፍላጎታችን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደሞዛችን እየተቆረጠብን ነው በሚል ነው። መምህራኑ ለይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር፣ ለጌዲዮ ዞንና ልክልሉ ትምህርት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ” ከ ሀምሌ 2005 ዓም ጀምሮ ለህዳሴ ግድብ የሚቆረጠው ገንዘባችን እኛ ያለፈቀድነውና ያልተስማማንበት በመሆኑ ጥቅምት 28፣ 2006 ጀምሮ  ስራችንን በአግባቡ እየሰራን የመብት ጥያቄያችንን ለሚመለከተው ሁሉ ስናቀርብ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እየከለከሉን ነው ሲሉ 18 የቻይና ኩባንያዎች አመለከቱ

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ 18 የቻይና ኩባንያዎች ቤጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በላኩት ደብዳቤ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቻይና ኩባንያዎች ከአንዳንድ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እንዳናገኝ እንቅፋት ፈጥረዋል ብለዋል። ኩባንያዎቹ የተሰማሩባቸው መስኮች የኃይል፣ የመስኖ፣ የመንገድና የንፁህ የመጠጥ ውኃ ግንባታዎች መሆናቸውን የዘገበው ጋዜጣው፣ በእነዚህ የመሠረተ ልማት ዘርፎች ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን ግጭቱ እንደቀጠለ ነው

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲሲቷ አፍሪካዊት አገር የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት በሺ የሚቆጠሩ የአገሪቱ ዜጎች ህይወት ከቀጠፈ በሁዋላ የሁለቱም ተፋላሚ ሀይሎች ተደራዳሪዎች በአዲስ አበባ ቢገኙም አሁንም ጦርነቱ ቀጥሎአል። በአዲስ አበባ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የሰላም ድርድር የተኩስ አቋም ስምምነት እንዲፈረም ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር በበኩላቸው የተኩስ ማቆም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ አለመሆናቸውን ገልጸዋል። በደቡብ ...

Read More »

በሶማሊያ በአንድ ታዋቂ ሆቴል ውስጥ ቦንድ ፈነዳ

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞቃዲሹ አየር ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው ጃዚራ ሆቴል ውስጥ በሁለት መኪኖች የተጠመዱ ቦንቦች ፈንድተዋል። ፍንዳታው ከመድረሱ በፊት በጠባቂዎች እና ፍንዳታውን ባደረሱት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። በአሁኑ ፍንዳታ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ አልታወቀም። ባለፈው ሳምንት በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ 11 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። አልሸባብ አሁንም የደቡብ የሶማሊያ አብዛኛውን ክፍል ተቆጣጥሮ ይገኛል። የኢትዮጵያ ጦር ...

Read More »

የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት ሊከሰሱ ነው

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሳዑዲ መንግስት የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸውን ኢትዮጽያዊያን ማባረሩን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ኤጀንሲዎች መካከል ከ100 በላይ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳትፈዋል የተባሉ ኤጀንሲዎች ላይ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን ከአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ በኢትዮጽያ በአጠቃላይ 470 የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች የሚገኙ ሲሆን 100 ያህሉ በህገወጥ የሰዎች ...

Read More »

ኢትዩጵያ ህጻናትን ወደ ውጭ በጉዲፈቻ ስም በመላክ ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑዋና መረጃዎች አመለከቱ

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንዳሳዩት በአፍሪካ ባለፉት 6 ዓመታት በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ ከተላኩት 34 ሺ 342 ህጻናት ውስጥ 63 በመቶ ወይም 21 ሺ 365 ሰዎችን በመላክ ቀዳሚ ናት። በሃገሪቱ በሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ፈቃድ የተሰጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉዳይ አስፈፃሚ የጉዲፊቻ ደላሎች ተበራክተዋል፡፡ በአብዛኛው ለጉዲፈቻ በሚቀርቡ ህፃናት የህይዎት ታሪክ ላይ የሚጻፈው ” ...

Read More »

ኢህአዴግ በሶስት ድርጅቶች ላይ አዲስ ዘጋቢ ፊልም እያዘጋጀ መሆኑ ተሰማ

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመሰራት ላይ ያለው አዲስ ፊልም ኦነግ ፤ ኦብነግ እና ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት የሚያወግዝ ነው። ኢህአዴግ በዚህ ሰአት ፊልሙን ለምን ለመስራት እንደፈለገ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። አንዳንዶች እንደሚገምቱት ከሆነ ግን ገዢው ፓርቲ በድርጅቶች እንቅስቃሴ ስጋት እየገባው ነው። እየተሰራ ባለው ፊልም ውስጥ ኢሳትንም ለመወንጀል እየታሰበ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል። ዘጋቢ ፊልሙ እስካሁን ባለመጠናቀቁ እና ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች ለድርድር ወደ አዲስ አበባ ቢያመሩም ጦርነቱ አልቆመም

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኤ ኤፍ ፒ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ለውይይት በአዲስ አበባ ይገኛሉ። ማቻር የሰላም ድርድሩን የተቀበሉት የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ አገራቸውና የኢጋድ አባላት በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ እጃቸውን በማስገባት አማጽያኑን እንደሚወጉ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ነው የሚለውን ዘገባ መሪው አስተባብለዋል። ለፕሬዚዳንት ሙሰቬኒ ...

Read More »