የአቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣን መልቀቅ ከድንበር ጋር የተያያዘ ነው ብሎ የአማራ ክልል ህዝብ እንደሚያስብ መንግስት ያስጠናው ጥናት አመለከተ

ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ኮሚኒኬሺን ጉዳዮች የህዝብ አስተያየት መረጃ ክፍል በቅርቡ ከስልጣናቸው በወረዱት አቶ አያሌው ጎበዜ እና አሁን በአስቸኳይ ጉባኤ በተተኩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ ባሰባሰበው የህዝብ አስተያየት እና ለመንግስት ባቀረበው የአሉታ እና አውንታ ትንታኔ እንደገለፀው የስልጣን መተካካቱ ዋና አላማ  መንግስት በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል ያለውን  የድንበር ውዝግብ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ያደረገው ነው ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው

ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስትና የተቃዋሚ ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ለድርድር ቢገኙም ቦር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አሁንም ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሰሞኑን በተቀሰቀሰው ጦርነት ኢትዮጵያን እንደተገደሉ የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሁለቱን ተፋላሚ ሀይሎች ፊት ለፊት በማገናኘት ጦርነቱ እልባት ያገኛል የሚል ተስፋ ቢያዝም እስካሁን ድረስ በተጨባጭ የታየ ነገር የለም። በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት በዋና ከተማው ...

Read More »

እስራኤል ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ነው

ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ እና የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት አፍሪካውያን የእስራኤል መንግስት ያወጣውን አዲስ ህግ እንዲቀይር፣ የታሰሩት እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም የስደተኞች ጉዳይ በጅምላ ከሚታይ ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ታይቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት የሚሉት እንደሚገኙበት በሰልፉ ላይ ተገኝቶ የነበረው አቶ አቦየ አስምረው ለኢሳት ገልጸዋል። “በሰላማዊ ሰልፍ ውጤት ...

Read More »

በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ረቡእ ታጣቂዎቹ  ከቀኑ 10 ሰአት ገደማ ወደ ከተማዋ በመግባት 3 ጠባቂዎችን በመግደልና አንደኛውን ታጣቂ መሳሪያውን በመቀማትና ልብሱን በማስወለቅ ” ሂድና ለአለቆችህ ንገር” በማለት ጉዳት ሳያደርሱበት መልቀቃቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ አንድ ድግን መትረጊስ፣ አንድ ላውንቸርና አንድ ባዙቃ ማርከው ወስደዋል። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው የደረሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎችን እየደበደቡ ...

Read More »

ኢህአዴግ በመንግስት ወጪ ለመጪው ዓመት ምርጫ ሕዝብ የማደራጀትና የመቀስቀስ ስራ ጀመረ

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ከ2007 አገር አቀፍ ምርጫ ጋር በተያያዘ በተለይ በአዲስአበባ ከተማ ሕዝብ ቅሬታ የሚያቀርብባቸውን የመልካም አስተዳደር፣ የሙስናና የልማት ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው። የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የ2006-2007 ዕቅድ አካል እንዲሆን በተደረገው ይህ ከመጪው ዓመት ምርጫ ጋር በቀጥታ የተያያዘው ዘመቻን በብቃት እንዲያስፈጽሙ ለክፍለከተማና ወረዳ አመራሮች ግልጽ መመሪያ ከመተላለፉም ባሻገር በአቅም ግንባታ ...

Read More »

የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለኢሳት ቃለምልልስ እንዳይሰጡ ታዘዙ

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣናቱ ማንኛውንም ቃለምልልስ ለኢሳት ቢሰጡ በአሸባሪነት ይከሰሳሉ። የባለስልጣኖች አንደኛው መገምገሚያም ለኢሳት መረጃ በመስጠት እንደሚወሰን ከኢህአዴግ የመረጃ ክፍል የደረሰን መረጃ ያመለክቷል። መመሪያው ለህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች፣ ለደህንነት ሰራተኞች፣ ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለ ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች መተላለፉ ታውቋል። የመንግስት ባለስልጣናት ለኢሳት መረጃ በመስጠት ድርጅቱን ህጋዊነት እያላበሱትና ሌሎችም ዜጎች አንዲናገሩበት እያደፋፈሩ ነው የሚል ምክንያት መሰጠቱ ታውቋል። ...

Read More »

አሜሪካ የኢምባሲ ሰራተኞቿን ከደቡብ ሱዳን እያስወጣች ነው

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና የተቃዋሚያቸው ሪክ ማቻር ወኪሎች ለድርድር  አዲስ አበባ በሚገኙበት በዚህ ሰአት ፣ የአሜሪካ መንግስት የኢምባሲ ሰራተኞች በሙሉ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ፣ የአሜሪካ የኢምባሲ ሰራተኞች በተዘጋጀላቸው አውሮፕላን ለቀው ይወጣሉ። ከጃንዋሪ 4 ጀምሮም ምንም አይነት አገልግሎት በኢምባሲው በኩል እንደማይሰጥ ግልጽ አድርጓል። የመንግስት ታጣቂዎች በተቃዋሚዎች የተያዙትን ቦታዎች ...

Read More »

የጣሊያን የድንበር ጠባቂዎች የ1 ሺ ሰዎችን ህይወት ማትረፋቸው ተገለጸ

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአብዛኛው የኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ዛምቢያ፣ ማሊና ፓኪስታን ዜጎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች መርከብ ጉዳት ከመድረሱ በፊት የጣሊያን ጠባቂዎች ደርሰው እንዳዳኑዋት ቢቢሲ ዘግቧል። ከሶስት ወራት በፊት ላምፓዱሳ እየተባለች በምትጠራዋ የጣሊያን ግዛት አቅራቢያ ከ400 በላይ ሰዎች መስጠማቸውን ተከትሎ የጣሊያን መንግስት ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል። የአሁኑ እርምጃም ይህን ትችት ለማምለጥ የተወሰደ ይመስላል። በአደጋው ከተረፉት መካከል 40 ...

Read More »

በግብጽ በተነሳ ተቃውሞ 6 ሰዎች ተገደሉ

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የሚገኙ የሙስሊም ብራዘርስ ሁድ ደጋፊዎች ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት 6 ሰዎች ተገድለዋል። ፓርቲው በበኩሉ የሞቱት ሰዎች 17 ናቸው ይላል። ግጭቱ የተነሳው ግብጽ መንግስት ፓርቲውን አሻበሪ ብሎ መፈረጁን ተከትሎ ነው። የፓርቲው መሪዎችና በቅርቡ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፈው ስልጣን ላይ የነበሩት ሙሀመድ ሙርሲ ወደ እስር ቤት ከተላኩ በሁዋላ ግብጽ ሰላም ለማግኘት ...

Read More »

በህወሀት ውስጥ የሚገኙ አክራሪ የሚባሉት ቡድኖች የመከላከያ አዛዥነቱ ከህወሀት እንዳይወጣ ለማድረግ ሲጥሩ መክረማቸው ተሰማ

ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ አዛዦች ለኢሳት እንደገለጹት የህወሀት ባለስልጣናት ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ለመተካት የተሻለ ቦታ ላይ የነበሩትን ጄ/ል አበባው ታደሰን አድማ ለማድረግ አስበዋል በሚል ሰበብ ማእረጋቸውን እንደያዙ የሚሰጣቸው ሃላፊነት እንዲቀነስና ከውድድር ውጭ እንዲሆኑ አድርገዋል። ለዚህም ስራ ጄኔራል ማሞ ሀይለማርያም እና ጄኔራል ሰሐረ መኮንን ተባባሪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሶስቱ ጄኔራሎች “ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ...

Read More »