የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ዜና እረፍት በክልሉ ውስጥ የተለያዩ ስሜቶችን ፈጥሯል።

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ45 አመቱ ጎልማሳ አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ ሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸው ከቆየ በሁዋላ ትናንት አርፈዋል። የአቶ አለማየሁን እረፍት ተከትሎ የኦህዴድ አባላትና የክልሉ ነዋሪዎች ስለአሟሟታቸው ሚስጢር የተለያዩ መላምቶችን እያቀረቡ በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል። አብዛኛው ህዝብ ግለሰቡ በተቃዋሚዎቻቸው ተመርዘው መሞታቸውን በማመን የአሟሟታቸው መንስኤ እንዲታወቅ ይፈልጋል። የኦህዴድ አባላትም በጉዳዩ ላይ እየተወያዩ ሲሆን ...

Read More »

ንግድ ሚኒስቴር ነጋዴዎች ለታክስ ህግ አይገዙም አለ

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካቲት 25 ቀን 2006 ዓ.ም. በ ንግድ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ  “አስመጪዎቹ  ታክስን በሚመለከቱ ለወጡ ሕጎች ተገዢ ባለመሆን፣ የሚያስመጧቸውን ዕቃዎች ከዋጋ በታች ደረሰኝ በመቁረጥ፣ ያለ ደረሰኝ በመሸጥ፣ በሚቆርጡት ደረሰኝ ላይ የገዢን ማንነት አለመጥቀስ፣ ግዢን በሒሳብ ውስጥ አለማካታት፣ ከንግድ ትርፍ የሚገኝን ገንዘብ መሬት ውስጥ መቅበር፣ ወደ ውጭ አገር ...

Read More »

በመንግስት የሚደገፉት የመጅሊስ አመራሮች እርስ በርስ እየተገማገሙ ነው

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደሚሉት በድሬዳዋ የተጀመረው በመንግስት የሚደገፈው የሙስሊም መሪዎች ግምገማ ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ይልቅ  ፖለቲካዊ ይዘቱ አመዝኖ ታይቷል። ከየክልሉ ተወክለው የመጡት መሪዎች አንዱ ሌላውን እንዲገልጽ በማስገደድ  ጭቅጭቆች መፈጠራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አክራሪነትን ለመቋቋም በሚል ህዝባዊ ንቅናቄ እንደሚጀምር አስታውቋል። በዚህ ንቅናቄ የሃይማኖትና ፖለቲካ አክራሪዎችን በየቀበሌው ያለውን ህዝብ በመሳተፍ ለመወጋት ...

Read More »

በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚገኘው ብአዴን የአቶ አለምነው መኮንንን ንግግር ለማስተባበልና ምንጩን ለማወቅ እየተዋከበ ነው

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አለምነው መኮንን በአማራው ህዝብ ላይ ያዘነቡትን ጸያፍ ስድብ ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባው ብአዴን፣ በክልሉ ፕሬዚዳንት በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ በራሳቸው በአቶ አለምነው መኮንን እንዲሁም በብአዴን ሊቀመንበርና በምክትል ጠ/ሚንስትር ደመቀ መኮንን አማካኝነት መግለጫ ቢሰጠም፣ ህዝቡን ለማሳመን ባለመቻላቸው፣ በወቅቱ በስብሰባው ላይ የተገኙ ጋዜጠኞችና ሌሎች ተወያዮች ቀርበው አቶ አለምነው አልተናገሩም እያሉ እንዲያስተባብሉ እየተደረገ ...

Read More »

አቶ አለማየሁ አቶምሳ ጥብቅ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንትነቱን ስልጣን ሳያስረክቡ እንዳስረከቡ ተደርጎ የተነጠቁት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ታይላንድ ባንኮክ ውስጥ በጥብቅ የህክምና ክትትል ወይም (ኢንቴንሲቭ ኬር ዩኒት) ውስጥ እንደሚገኙ ኢሳት አረጋግጧል። ግለሰቡ ያለመሳሪያ ድጋፍ በራሳቸው መተንፈስ እንደማይችሉ ፣ ሰዎችን እንደማያናግሩና በዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ እኩለቀን ላይ አንድ የሆስቲታሉ ሰራተኛ ለኢሳት ተናግረዋል። አቶ አለማየሁ ከኦህዴድ የምክር ቤት ...

Read More »

በሰሜን ወሎ በመርሳ ከተማ በህዝብና በፖሊስ መካከል በተደረገ ግጭት ሁለት ሰዎች ተጎዱ

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግጭቱ የተነሳው በህገወጥ መንገድ ተስርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ የመዘጋጃ ሰራተኞች እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ተከትሎ ነው። ህዝቡ ድንጋይና ዱላ በመያዝ ፖሊሶችን ደብድቦ ያባረረ ሲሆን፣ ፖሊሶቹ ተደራጅተው በመምጣት ሁለት ሰዎችን በጥይት መትተው የተወሰኑትን ደብድበው አስረዋል። ፍጥጫው ዛሬም ደረስ የቀጠለ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪ ቤቶቻችን አይፈርሱም በማለት በአቋሙ እንደጸና ነው። የቆሰሉት ሰዎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ...

Read More »

በቁጫ ወረዳ አንድ ወጣት ራሱን እናቱንና ከብቶቹን በእሳት አጋየ

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ በቦላ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ9ኛ ክፍል ተማሪ ኢዮብ ኢማን  የካቲት 21 ቀን 2006 ዓም ከምሽቱ 3 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ ራሱን ጨምሮ እናቱን፣ 8 የቀንድ ከብቶችንና ሌሎች ንብረቶችን በእሳት አጋይቷል። ወጣቱ የካቲት 3 ቀን የቁጫ ወረዳ ባህላዊ ዘፈን ከጓደኞቹ ጋር እየዘፈነ በሄደበት ወቅት አንድ የፖሊስ ባልደረባ ” ...

Read More »

በኬንያ የታክሲ አሽከርካሪዎች አድማ መቱ

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአድማው መነሻ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የተጣለውን አዲስ የፓርኪንግ ክፍያ ተከትሎ ነው። ባለ ታክሲዎቹ መኪኖቻቸውን ለማቆም ከፍተኛ የሆነ ከፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል። ባለ ታክሲዎች ባደረጉት አድማ አብዛኛው ሰራተኛ ብእግሩ ስራ ለመግባት ተገዷል። ባለስልጣናቱ በበኩላቸው እርምጃው በናይሮቢ የሚታየውን መጨናነቅ ለመቀነስ ነው ይላሉ።

Read More »

በጅቡቲ መንገድ ላይ በአድማ ቆመው የነበሩ ከባድ መኪኖች ዛሬ ስራ ጀመሩ

የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ የከባድ መኪና ሾፌሮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሶስት ቀናት በፊት አንድ ሾፌር እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደሉን  ተከትሎ  የተጀመረው አድማ ዛሬ ተጠናቆ መኪኖች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን የሆኑት አቶ ካሳሁንና ኮሚሽነር ግርማይ ከሾፌሮች ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ ገዳዩን አድነው እንደሚይዙት ቃል በመግባት ሾፌሮች ስራ እንዲጀምሩ መክረዋል። ሾፌሮች በበኩላቸው ባልደረባቸው የተገደለበት ሁኔታ እጅግ ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የስምሪት ሃላፊ ሾመ

የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረዳት ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 በመጥለፍ ጄኔቫ በማሳረፍ ጥገኝነት መጠየቁን ተከትሎ፣ ካፒቴን ዮሃንስ ሃይለማርያምን አዲስ የስምሪት ሃላፊ አድርጎ ሾሟል። የቀድሞው ሃላፊ ካፒቴን ደስታ ዘሩ ስልጣናቸውን በምን ሁኔታ እንደለቀቁ ባይታወቅም፣ ስልጣናቸውን የለቀቁት በጠለፋው ማግስት መሆኑ ጉዳዩ ከሃይለመድህን አበራ ጠለፋ ጋር ሳይያያዝ አይቀርም የሚሉ አስተያየቶች ይቀርባሉ። በሌላ ...

Read More »