የመከላከያ ሰራዊት በቦዲዮች ላይ ተኩስ ከፍቶ በርካታ ሰዎችን ማቁሰሉን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ

መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጋቢት 24 ቀን በቦዲዎችና በኮንሶዎች መካከል ለአንድ ወር ያክል የቆየውን ግጭት ለማብረድ በሚል ወደ አካባቢው የተጓዘው የመከላከያ ሰራዊት በቦዲዎች ላይ በመትረጊስ የታገዘ ተኩስ በመክፈቱ በርካታ ነዋሪዎች መቁሰላቸውን ከእነዚህም ውስጥ 17 አሮጊቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች በሃና ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ጂንካ የሚገኘው የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ጽ/ቤት ለኢሳት ገልጿል። የመከላከያ ሰራዊቱ የወሰደውን ...

Read More »

በመጪው እሁድ በሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላት ታሰሩ

መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳደር የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃለፊ ሆኑት አቶ ያሬድ አማረ ለኢሳት እንደገለጹት ምንም እንኳ የተወሰኑ ሰዎች የታሰሩ ቢሆንም፣ ቅስቀሳው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ሀብታሙ ታምሩ፣ አሸናፊ ጨመረዳ እና ደራሲ መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን የቅስቀሳ ወረቀቶችን ሲበትኑ ተይዘው የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል። ለገሃር ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ደግሞ አክሊሉ ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ውይይት አደረገ

መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-” ኢትዮጵያ መረጃ የሚያወጡትና ጋዜጠኞችን ስሚ” በሚል ርእስ የአውሮፓ ህብረት ሶሻሊስቶችና ዲሞክራቶች ከአለም የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ከሆነው ሲፒጄ ጋር በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ በቃሊቲ እስር ቤት ከአንድ አመት በላይ ታስሮ የተለቀቀው ስዊድናዊው ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብየና በኦጋዴን የተካሄደውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚያጋልጥ መረጃ ይዞ የወጣው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን፣ የአውሮፓ ህብረት ...

Read More »

አንድ የአሜሪካ ወታደር 3 ባልደረቦቹን ግደሎ 16ቱን አቆሰለ

መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢቫን ሎፔዝ የተባለው የ34 አመት ተጠርጣሪ ወታደር ቴክሳስ ውስጥ በሚገኝ የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ነው። ገዳዩ በኢራቅ ሲያገለግል የነበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በድርጊቱ በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል። ገዳዩ ራሱን ማጥፋቱም ታውቋል።

Read More »

በአዋሳ ታቦር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተነሳ ግጭት ተማሪዎች ተጎዱ

መጋቢት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቋንቋ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በተነሳው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚወጡ ተማሪዎችን ሲደበድቡ የታዩ ሲሆን፣ በውስጥ ያሉ ተማሪዎችም እንዲሁ ድንጋይ ሲወረወሩ መታየታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ግጭቱ ተባብሶ በመሄዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጥይቶችን በተደጋጋሚ ተኩሰዋል። ታቦር ትምህርት ቤት መዘጋቱንም ለማወቅ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ህዝብ ለቀረበት ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ አንድነት ፓርቲ ጠየቀ

መጋቢት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹በህገ ወጥ መንገድ የሚቀለበስ ሰላማዊ የትግል ስልት ባለመኖሩ የአዲስ አበባ ህዝብ ለቀረበለት የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ምላሹን እንዲሰጥ ጠይቋል። የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ህገ ወጥ ደብዳቤ በመጻፍ ሰልፉን ማከናወን አትችሉም ማለቱ ከህግ በላይ መሆኑን እንደሚያሳይ ፓርቲው ገልጿል። መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንዲደረግ ...

Read More »

የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ቤት ውሎ የተከሳሾችን ጥንካሬ ያሳየ ነው ተባለ

መጋቢት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተከሳሽ ቃላቸውን በመስጠት ላይ ያሉት የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት በፍርድ ቤቱ ውስጥ የሚያሰሙት ንግግር የብዙዎችን ታዳሚዎች ቀልብ እየሳበ መምጣቱን እና በእስረኞች ላይ የሚታየው ጽናት የሚያስገርም መሆኑን ችሎቱን የሚከታተሉ ታዳሚዎች ገልጸዋል። ትናንት ቃላቸውን የሰጡት የኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ የሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ  ትግል በዝርዝር አቅርበዋል። በእስር ቤት ውስጥ የደረሰባቸውን በደልም የታዳሚውን ስሜት ...

Read More »

በካይሮ የፖሊስ አዛዡ ተገደሉ

መጋቢት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግብጽ የካይሮ ዩኒቨርስቲ አካባቢ በፈነዱ 3 ቦንቦች  አንድ የፖሊስ አዛዥ ሲገደሉ ሌሎች አምስት ሰዎችም ቆስለዋል።የጥቃቱ አላማ በፖሊሶች ላይ ማነጣጠሩን የሃገሪቱ ቴሌቪዥን ገልጿል። የእስላማዊ ወንድማማቾች ፓርቲ ህገወጥ ተብሎ እንዲፈርስ ከተደረገና የፓርቲው ሊቀመንበርና ከዚሁ ፓርቲ በመውጣት ግብጽን ሲመሩ የነበሩት ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ከታሰሩ በሁዋላ በግብጽ ተደጋጋሚ ፍንዳታዎች እየደረሱ ነው፡፡ ወታደራዊ ስልጣናቸውን የለቀቁት ፊልድ ...

Read More »

የኤርትራ መንግስት ከእኛ ጋር ለመታረቅ ከፈለገ ከጉያችን ያሉ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ምን ይሆናሉ ብለን አንሰጋም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ

መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ጌታቸው አረዳ እንደተናገሩት ” የኤርትራ መንግስት ሃሳቡን ቀይሮ ወደ ሰላም ቢመጣ የኢትዮጵያ መንግስት ችግር የለበትም። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ከጉያችን ስላሉ ምን እንሆናለን የሚል ስጋት የለብንም” በማለት ተናግረዋል። የታጠቁ የኤርትራ ሃይሎች እርምጃ የማይወስዱት በድንበር አካባቢ የኤርትራ ሰራዊት በብዛት ስላለ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ዳይሬክተሩ፣ የኤርትራ ...

Read More »

ውሃ ፣መብራት፣ቴሌ አሁንም ሕዝቡን እያስመረሩት ነው

መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ የመጠጥ ውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሁም የሞባይልና የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቆራረጥ በያዝነው መጋቢት ወር ተባብሶ በመቀጠሉ ነዋሪዎች ለአላስፈላጊ ኪሳራ ከመዳረጋቸው ጋር ተያይዞ በነዋሪው ዘንድከፍተኛ ምሬት መፍጠሩን ዘጋቢያችን ገልጿል። በያዝነው  ወር የኤሌክትሪክ ኃይል ቢያንስ በሁለት ቀን አንድ ጊዜ ለሰዓታት የሚጠፋበት ሁኔታ በተደጋጋሚ መስተዋሉን ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን በዚህም ምክንያት ለአንድ ፍሬ ...

Read More »