የመንግስት የ5 አመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ የኑሮ ውድነቱን እንዳባባሰው ተገለጠ

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚታየው የኑሮ ውድነት የታችኛውና መካከለኛ ገቢ አለው የሚባለው የመንግስት ሰራተኛው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እየሆነ ነው። ጤፍ በአዲስ አበባ በኩንታል እስከ 1700 ብር በመሸጥ ላይ ነው። ዘይትና ስኳር ደግሞ ጭራሽ ከገበያ ጠፍተዋል። ለአንዳንድ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በየወሩ ስኳርና ዘይት ለማከፋፋል ሙከራ እየተደረገ ነው። እስከዛሬም መንግስት ስንዴ ከውጭ እያስመጣና ገበያውን እየደጎመ ...

Read More »

በሚኒሶታ ለኢሳት ቴሌቭዥን የተሳካ የገቢ ማሰባሰብ ተደረገ

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዘ ሀበሻው ሮቤል ሔኖክ እንደዘገበው  የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንን በገንዘብ ለማጠናከር በሚል ዋና ዓላማ በሚኒሶታ የተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተካሄዷል። አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነን፣ አባ ወልደተንሳኤን እና አባ ገብረማርያምን፣ እንደዚሁም ተወዳጁን ድምጻዊ ተሾመ አሰግድን የክብር እንግዶች በማድረግ የተዘጋጀው ይኸው የራት ምሽት ላይ መድረኩን በሚመራው በጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ ነበር የተከፈተው። ...

Read More »

የአዲስ አበባ መምህራን የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እንቅስቃሴዎችን ጀምረዋል

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ የተደረገውን የደሞዝ ጭማሪ የተቃወሙ መምህራን የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ ውይይት መጀመራቸው ታውቋል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ መምህር እንዳሉት መምህራን አሁን የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም መሰረታዊ የሚባል የደሞዝ ጭማሪ የጠየቁ ቢሆንም፣ መንግስት የሰጠው መልስ ግን መምህራንን ለበለጠ ጉዳት የሚዳርግ ነው። የኑሮ ውድነቱ ብቻውን መምህራን ለተቃውሞ እንዲነሱ አድርጓቸዋል ያሉት መምህሩ፣ ይህም በመሆኑ መምህራን ...

Read More »

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በሙስና የተዘፈቀ መሆኑ ተነገረ

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወ/ሮ እሌኒ ገብረመድህን የሚመሩት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በሙስና የተዘፈቀ መሆኑ ተመለከተ ወንዶሰን መዝለቂያ ከአለም ባንክ ያገኙዋቸውን መረጃዎች በማያያዝ ባወጡት የምርመራ ዘገባ የሸቀጦች ገበያ ድርጅት በሙስና መዘፈቁን የሚያሳዩ ግልጽ መረጃዎች ቢኖሩም፣ ሙስናን እዋጋለሁ የሚለው የጸረ ሙስና ኮሚሸንም ሆነ ጉዳዩን ጠንቅቀው የሚያዉቁት አቶ መለስ ዜናዊ ምንም እርምጃ አልወሰዱም። የአለም ባንክ ወ/ሮ ኢሌኒ ለሚመሩት  ...

Read More »

የዋጋ ንረቱ መንስኤ አርሶ አደሩ በአፍር ጥበቃ ላይ በመሰማራቱ ነው ተባለ

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጤፍ የችርቻሮ ዋጋ የጨመረባቸው ዋነኛ ምክንያቶች በኮንትሮባንድ ከሀገር እየወጣ በመሆኑና አርሶ አደሩም በአብዛኛው በአፈር ጥበቃ ሥራ ከመሰማራቱ ጋር በተያያዘ ምርቱን ወደ ገበያ ይዞ በመውጣቱ መሆኑን የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓሊ ሲራጅ መግለጣቸውን ሰንደቅ ዘግቧል። አቶ ዓሊ የጤፍ ምርት ዋጋ እንዲቀንስ መንግስት በአካባቢና አፈር ጥበቃ ላይ የተሰማራው ገበሬ ምርቱን ወደ ገበያ ይዞ እንዲወጣ ...

Read More »

በወጣቶች እንቅስቃሴና በሰብኣዊ መብት ረገጣ የአንድ ወር ሪፖርት ቀረበ

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እኤአ ከየካቲት 9 እስከ መጋቢት 9/2012 በክልሉ ዉስጥ ስለነበረዉ የወጣቶች እንቅስቃሴና በመንግስት በኩል ስለተወሰደዉ የመብት ረገጣ የሚገልፀዉን የአንድ ወር ዝርዝር ሪፖርት ያወጣዉ የኦሮሚያ ወጣቶች ንቅናቄ  የተባለዉ ድርጅት ነዉ። በመንግሰት ጥቃት የተፈፀመባቸዉን የኦሮሞ ተወላጆች በሙሉ በስም በመጥቀስ ድርጅቱ ባወጣዉ ሪፖርት፤ በኦሮሚያ  ምእራብ ሸዋ ዞን በአዳ-በርጋ ወረዳ አነስተኛ ገበሬዎችን ከመሬታቸዉ በማፈናቀል ከኢትዮጵያ መንግሰት ጋር ...

Read More »

አንድ ተማሪ ከፖሊስ በተተኰሰ ጥይት ቆስሎ ወደ ሕክምና ተወሰደ

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዝቋላ ገዳም ቃጠሎውን ለማጥፋት በተሰበሰቡ ወጣቶች እና በኦሮሚያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ መካከል በተቀሰቀሰው አለመግባባት አንድ ተማሪ ከፖሊስ በተተኰሰ ጥይት እግሩ ላይ ቆስሎ ወደ ሕክምና መወሰዱን ደጀሰላም ዘገበ ወጣቶቹ ቃጠሎውን አስመልክቶ በቀጥታ ስርጭት ዘገባ ማስተላለፍ ሥራ ላይ የነበረውን ጋዜጠኛ በመቃወማቸው ጸቡ ተፈጥሯል። የዐይን እማኞችን ጠቅሶ ድረገጹ እንደዘገበው  ጋዜጠኛው እሳቱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የሚገልጽ ዘገባ ...

Read More »

የዝቋላ ገዳም ደን በእሳት እየተቃጠለ ነው

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አካባቢ የሚገኘው ደን በመንደድ ላይ መሆኑን የገዳሙ አባቶች ተናገሩ። ባለፈው አርብ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የተነሳው ቃጠሎ  የዝቋላ አቦ ቤተክርስቲያንን ሊያቃጥላት ይችላል ተብሎ የተፈራ ቢሆንም፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ደረስ የእሳቱ መጠን የቤተክርስቲያኑንና የገዳሙን ህልውና ወደ ማይፈታተንበት ደረጃ ቀንሶአል። በካባቢው በእሳት ማጥፋት ላይ ...

Read More »

በጋምቤላ የጸጥታ ማስጠበቁ ስራ ለፌደራል ፖሊስ ተሰጠ ምክር ቤቱም ተከፍሎአል

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ የጸጥታ ማስጠበቁ ስራ ከክልሉ መንግስት ተወስዶ ለመከላከያ እና ለፌደራል  ፖሊስ ተሰጠ  ምክር ቤቱም ተከፍሎአል በጋምቤላ የሚታየው የጸጥታ መደፍረስ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ስቦ ቆይቷል። የኢሳት ዘጋቢዎች  በክልሉ ያለውን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ሲዘግቡና ለህዝብ ይፋ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በኢትዮጵያ የምእራብ ጠረፍ የምትገኘዋ ጋምቤላ በስልጣን ላይ ያለው የህወሀት መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ሰላምና መረጋጋት ርቋት ...

Read More »

ህወሀት የመለስና የሚስቱ ፓርቲ እየሆነ ነው ተባለ

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት የአመራር አባል ይህን የተናገሩት አትላንታ ተዘጋጅቶ በነበረው ዝግጅት ላይ ነው። አቶ ስየ ከተሰብሳቢው ጥያቄ በቀረበላቸው ጊዜ ”  በአጠቃላይ ህወሃት የመስራች ወይም የአባላቱ ፓርቲ አይደለም። እባካችሁ የትግራይም ነው አትበሉ። የቤተሰብ ፓርቲ  እየሆነ ነው። ከዚያም እየቀጠነ የመለስ እና የሚስቱ የአዜብ ፓርቲ እየሆነ ነው ያለው።” በማለት ተናግረዋል። ኦህዴድ ወይም ብአዴን የሚለው ነገር ምርጫ ለመስረቅ ካልሆነ ...

Read More »