ሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤት ከህዝብ አግለልጋይነቱ ወጥቶ የፓርቲ ስራ ማሰፈፀሚያ እየሆነ ነው ተባለ፡፡

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በሚመራው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ ውይይት ሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ፣ ለህዝብ ተቋማት እና የመንግስት ቢሮዎች የአሰራር ስርዓቱ ውጤታማና  ቀልጣፋ እንዲሆኑ ከማገዝ ይልቅ በፖለቲካ አሰተሳሰብ እና የፓርቲ ስራዎችን በመስራት የተጠመደ በመሆኑ በርካታ የሲቪል ሰርቪስ ስራዎች ሳይሰሩ እንደሚቀሩ ተመልክቷል፡፡ ተገልጋዮች በአግልግሎት እጦት እየተማረሩ እና እየተሰቃዩ መሆናቸውን እየገለጹ መሆኑን ...

Read More »

በአማራ ብሄር ላይ እየደረሰ ያለው በደል ኢትዮጵያዊነታችንን እየተፈታተነ ነው ሲሉ የአገር ሽማግሊዎች ገለጹ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በክልሉ ነዋሪዎች ላይ የፈጠረው ጥላቻ እና እየወሰደ ያለው እርምጃ የኢትዩጵያዊ ማንነታቸውን እየተፈታተነው እንደመጣ የክልሉ የሀገር ሺማግሌዎች ለመስተዳድሩ ባለስልጣናት አቤቱታ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡ የአገር ሽማግሌዎቹ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ባስገቡት ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው በቅርቡ በባህር ዳር ከተማ በህገወጥ መንገድ ተገነቡ የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ በተወሰደ እርምጃ አራት ንፁሃን ዜጎች መገደላቸው አሳፋሪ መሆኑን ጠቅሰዋል። ...

Read More »

የአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ እናቶችን እና ለጋ አራሶችን ጤና ለማሻሻል 40 ሚልዮን ዩሮ ለገሰ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውሮፓ ኅብረት “በኢትዮጵያ በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች የማዋለድ አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት በሚሰኘው ፕሮጀክት በኩል ለፌደራል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ40 ሚልዮን ዩሮ ልገሳ ማበርከቱን አስታውቋል፡፡ ከአውሮፓ ኅብረት የተበረከተው አዲሱ ልገሳ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የእናቶችን ጤና እና የለጋ አራሶችን ክብካቤ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ይውላል፡፡ ከዚህ ልገሳ ውስጥ፤ 20 ሚልዮን ዩሮ ያህሉ ለፌደራል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በተመድ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ደጋፊዎች ሳይሆኑ አይቀርም የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች መጠለያ ግቢ ውስጥ በሰነዘሩት ጥቃት ከ30 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዚህ በሁዋላ ጥቃት ቢፈጸም አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። በአገሪቱ የሚታየው ጦርነት ወደ ጎሳ ግጭት ያመራል ተብሎ እየተፈራ ነው። ፕ/ት ሳልቫኪር በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ የሰላም ...

Read More »

በጭልጋ ወረዳ ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ ጉዳት መደርሱ ተሰማ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ በአይከል ከተማ ከቅማንት ብሄረሰብ የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳ የተማሪዎች ተቃውሞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች በአድማ በታኝ ፖሊሶች ተደብድበው ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወደ አካባቢው ሄዶ የተለያዩ መጠይቆችን በማድረግ በብሄረሰቡ ለቀረበው ጥያቄ መልስ ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ወቅት ችግሩ መነሳቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ፌዴሬሽኑ ...

Read More »

በጃቢጠህናን ከአምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ ጎጃም ዞን በጃቢጠህናን ወረዳ የሆዳንሽ ቅዱስ ገብርኤል ቀበሌ ኗሪዎች የሆኑ ከአምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ህገ-ወጥ ግንባታ በሚል ቤታቸው እንዲፈርስ የወጣውን ትዛዝ በመቀዋወም አደባባይ ወጥተዋል፡፡ የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገው የወረዳው ከፍተኛ ባለስልጣናት ሚያዝያ 5 ፣ 2006ዓ.ም የቀበሌውን ህዝብ ሠብሰብው ከ808 በላይ ህገወጥ ቤቶች ይፈርሳሉ በማለት ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ ነው። ” የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ...

Read More »

የሸቀጦች ዋጋ አሁንም ከፍተኛ ነው ሲሉ ሸማቾች ገለጹ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ በሾላ እና በሳሪስ ገበያዎች የሸቀጦች ዋጋ መጠነኛ መረጋጋት ቢታይባቸውም ከሕዝቡ የመግዛት አቅም ጋር ሲነጻጸር አሁንም ዋጋቸው ውድ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገርናቸው ሸማቾች ገልጸዋል፡፡ በገበያዎቹ  ተዘዋውሮ የተመለከተው ዘጋቢያችን የፈረንጅ ሽንኩርት በኪሎ ከ12- 14 ብር፣ የአበሻ ሽንኩርት ከ20-26 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት ከ40-45 ብር በመሸጥ ላይ መሆናቸውን ገልጿል። ቅቤ ለጋ የሚባለው በኪሎ ከ170-190 ፣ መካከለኛ ከ170-180፣ ...

Read More »

ህገ ወጥ አሰራሮችን ያጋለጡ መምህራን ታሰሩ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ስሙ ቤላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የህብረት ፍሬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የሆኑት መ/ር ጥላሁን በዙ እና መ/ር አዳም ዘውዱ በት/ቤቱ እየተከናወነ ያለዉን ህገ-ወጥ አሰራር በመቃወማቸው እንዲሁም ለፌደራሉ ፀረ-ሙሰና ኮሚሽን ጥቆማ በማድረጋቸው፣ ወንጀል ሰርተዋል በሚል ከተጠረጠሩት ጋር አብረው እንዲታሰሩ መደረጉን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ መምህራን ገልጸዋል። ...

Read More »

በናይጀሪያ ከ100 በላይ የሚሆኑ ታዳጊ ሴት ተማሪዎች በታጠቁ ሀይሎች ከትምህርት ቤታቸው ተጠልፈው ተወሰዱ።

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ እንደዘገበው  ታጣቂዎቹ  ሴት ተማሪዎቹን በሰሜን ምስራቅ ናይጀሪያ ወደሚገኝ  ሩቅ ስፍራ ነው ይዘዋቸው የሄዱት። የናይጀሪያ ወታደራዊ ሀይል  ክስተቱን ተከትሎ በሰጠው መግለጫ  ከተጠለፉት 129 ታዳጊ ሴቶች ስምንቱ ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹ አምልጠው መምጣታቸውን ቢገልጽም፤ የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ግን አሁንም በርካታ ልጆች መጥፋታቸውን ነው እየተናገሩ ያሉት። ድርጊቱን የፈፀመው “ቦኮ ሀራም” የተሰኘው እስላማዊ ቡድን መሆኑን የገለፁት የሀገሪቱ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ የሚካሄደውን ጦርነት በመሸሽ በእየቀኑ እስከ 1 ሺ ሰዎች በጋምቤላ አካባቢ ወደ ሚገኙ የኢትዮጵያ ግዛቶች እየገቡ ነው። ስደተኞቹ ረጅሙን መንገድ በማቋረጣቸው በምግብ እና በውሃ እጥረት የተጎዱ መሆናቸውን የጋምቤላ አካባቢ ነዋሪዎች ይናገራሉ። እልባት ያልተገኘለት የደቡብ ሱዳን ጦርነት በሚቀጥሉት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከአገሪቱ የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።የደቡብ ሱዳን መንግስት ሰሞኑን የነዳጅ ከተማ የሆነቸውን ቤንትዩን የተቆጣጠሩት ...

Read More »