መድረክ በርካታ ህዝብ በተገኘበት የተሳካ ወይይት አደረገ

የካቲት 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እሁድ እለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጽ/ ቤት አዳራሽ በአዲሱ የከተማ መሬት አዋጅ ላይ ህዝባዊ ውይይቴ ማካሄዱን በስፍራው የተገኘው  ዘጋቢያችን ገልጧል። ውይይቱን ዶ/ር መረራ ጉዲና የመሩት ሲሆን የመድረክ የአመራር አባል አቶ ገብሩ አስራት እና በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚዎች ተወካይ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በጥናት ላይ የተመሰረተ የውይይት መነበሻ ሃሳቦችን አቅርበዋል፡፡ አቶ ገብሩ ...

Read More »

ስዊድናውያንኑ ጋዜጠኞች ላይ መንግስት የያዘው የተለየ አቋም የለም ሲሉ አቶ በረከት ስምዖን ተናገሩ

የካቲት 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው የ 11 ዓመት እስራት በተበየነባቸው ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይ መንግስት የያዘው የተለየ አቋም የለም ሲሉ አቶ በረከት ስምዖን ተናገሩ። የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትርና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን ጋዜጠኞቹ ይቅርታም ቢጠይቁ በቅርቡ ሊፈቱ እንደማይችሉ የጠቆሙት፤አቶ መለስ ፓርላማ ቀርበው ጋዜጠኞቹ ይቅርታ ከጠየቁ ሊፈቱ እንደሚችሉ ፍንጭ መስጠታቸው በዓለማቀፍ ብዙሀን መገናኛዎች ይፋ በሆነ ...

Read More »

ዛምቢያ የአፍሪካ ዋንጫን ወሰደች፣ ህዝቡ ደስታውን መቆጣጠር አልቻለም

የካቲት 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-10 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ዛምቢያ በሊበርቪሌ ጋቦን ተዘጋጅቶ የነበረውን የአፍሪካ ዋንጫ አይቮሪ ኮስትን በፍጹም ቅጣት ምት 8 ለ7 በሆነ ውጤት አሸንፋ ዋንጫውን ወስዳለች። የዛምቢያው አሰልጣኝ ሄርቪ ሪናርድ  ዋንጫ በ1993 በአውሮፕላን አደጋ ለተሰውት የዛምቢያ ተጫዋቾች መታሰቢያ እንደሚሆን ተናግረዋል። ከ19 አመት በፊት የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ወደ ሴኔጋል ሲያመራ የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ  በተዘጋቸበት በጋቦን  በተከሰተ ...

Read More »

መድረክ በሊዝ አዋጁ ዙሪያ በጠራው ስብሰባ ላይ በርካታ ህዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት አንድነት ፓርቲ በጠራው ውይይት ላይ የተገኘው ህዝብ ከአዳራሹ አቅም በላይ መሆን፣ የነገውን የመድረክ ስብሰባ የአዘጋጁትን ወገኖች አሳስቦዋቸዋል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የመድረክ አባል ለኢሳት እንደተናገሩት በቀድሞው ቀበሌ 42 በአሁኑ ወረዳ 5 የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ በርካታ ህዝብ እንደሚገኝ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ የራሱን ሰዎች አብዛኛውን ቦታ እንዲይዙት ...

Read More »

በአወልያ የሚገኙ ሙስሊሞች ተቋውሞአችንን በመላው መስጊዶች ማሸጋገር እንችላለን ሲሉ አስጠነቀቁ

የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወልያ የሚገኙ ሙስሊሞች ለሰላም ስንል እንጅ፣ ተቃውሞዋችንን በአንዋር መስጊድ እና በመላው አገሪቱ በሚገኙ መስጊዶች ማሸጋገር እንችላለን ሲሉ አስጠነቀቁ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የአርብ ስግደትን ለማካሄድ በአወልያ በተገኙበት ሰአት እንደተናገሩት መንግስት ለጥያቄቸው መልስ የማይሰጥ ከሆነ ተቃውሞውን በመላ አገሪቱ በሚገኙ መሲኪዶች ሁሉ እንደሚያሸጋግሩት  አስጠንቅቀዋል። ችግሩን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ተደራድረው መፍትሄ እንዲፈልጉ ከተወከሉት መካከል አንዱ የሆኑት አቡበክር ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በሳውዲ አረቢያ ለታሰሩ ወገኖቻቸው በቂ ትኩረት አልሰጠም ተባለ

የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኮንሰርን ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው፣ በእስር ላይ የሚገኙት 35 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉላቸው ቢጠይቁም፣ የኢምባሲው ሰራተኞች ግን ለጉዳያቸው ትኩረት ሊሰጡ አልፈለጉም። እስረኞቹ እንደሚሉት አንድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በጎበኛቸው ወቅት በአራት ቀናት ውስጥ ተመልሶ እንደሚመጣ ቃል ቢገባላቸውም ፣ እስከ ዛሬ ዘወር ብሎ እንዳላያቸው ተናግረዋል። በጂዳ ኢምባሲ ጽህፈት ቤት ሰራተኛ  የሆኑት መርዋን ...

Read More »

በሶሪያ አንድ የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ጄኔራል ተገደሉ

የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሶሪያ የመከላከያ ሆስፒታል አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጄኔራል ዶ/ር ኢሳ አል ኮሊ የተገደሉት በታጠቁ አሸባሪዎች ነው ሲሉ የመንግስቱ የመገናኛ ኤጀንሲ ዘግቧል። በሶሪያ  ህዝባዊ አመጽ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ከፍተኛ የወታደራዊ አዛዥ ሲገደሉ ብርጋዴር ጄኔራል ዶ/ር ኢሳ አል ኮሊ የመጀመሪያ ናቸው። የሶሪያ መንግስት ወታደሮች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሆምስ በከፈቱት ጥቃት ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የመገናኛ ብዙሀን ...

Read More »

ሰሞኑን በጦርነት ወሬ ሲታመሱ የቆዩት ደቡብና ሰሜን ሱዳን አንዱ በሌላው ላይ ጦርነት ላለመጫር ተስማሙ

የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሁለቱ አገሮች ስምምነቱን የፈረሙት በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በታቦ ምቤኬ አደራዳሪነት በአዲስ አበባ ነው። ሁለቱ አገሮች አንዱ የሌላውን ሉአላዊነት ለማክበር ተስማምተዋል፤ አላስፈላጊ ከሆነ ፕሮፓጋንዳም ራሳቸውን እንደሚያቅቡ ፈርመዋል ሲሉ ታቦ ምቤኪ ተናግረዋል። በቅርቡ ከነዳጅ ዘይት ጋር በተያያዘ የተነሳው አለመግባባት ለድርድር አለመቅረቡም ተመልክቷል። ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል አልፎ ጅቡቲ የሚደርስ የነዳጅ ቧንቧ ለመዘርጋት ስምምነት መፈረሙዋ ይታወሳል።

Read More »

በሆሳዕና በተፈጠረው የውሀ እጥረት ነዋሪዎቹ አደጋ ላይ መውደቃቸውን ገለጡ

የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት በከተማው በተከሰተው የውሀ እጥረት የተነሳ የአካባቢው ህዝብ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቋል። ውሀ ከጠፋ ወራት ማስቆጠራቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች በተለይ ባለፈው ሳምንት መብራት እና ውሀ በአንድ ላይ  በመጥፋቱ የህዝቡን ችግር አባብሶታል። ህዝቡ የወንዝ ውሀ ለማግኘት 8 ኪሎሜትር ድረስ መጓዝ ግድ እንደሆነበት ነዋሪዎች ይናገራሉ። 20 ሊትር የወንዝ ውሀ በ10 ብር ለመግዛት መገደዳቸውንም ያክላሉ ...

Read More »

በታሪካዊነቱ የሚታወቀው ዋልድባ ገዳም ከመንግስት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገባ

የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአድርቃይ ወረዳ የሚገኘው የዋልድባ ገዳም አካባቢ ለሸንኮራ አገዳ ምርት ይፈለጋል በሚል ምክንያት መታጠሩ መነኮሳቱን ጨምሮ የአካባቢውን ህዝብ አስቆጥቷል። በታሪካዊነቱ የሚታወቀው የዋልድባ ገዳም ከጥንት ጀምሮ በይዞታነት የያዘው መሬቱ በግድ እንዲታጠር መደረጉ ያበሳጫቸው መነኮሳትና ህዝቡ ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጀምሮ ላሉ ባለስልጣናት አቤት ቢልም የሚሰማው አላገኘም። ሰሞኑን ውዝግቡ እየተካረረ መምጣቱን፣ መንግስት ውሳኔውን ካላስተካካለ ...

Read More »