ዘመነ ካሴ በቀረረበበት የሽብርተኝነት ክስ መልስ ሰጠ

ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የአመራር አባልና የቀድሞው የአማራ ክልል ወጣቶች ሊቀመንበር ዘመነ ካሴን ጨምሮ 10 ወጣቶች በተከሰሱበት የሽብረተኝነት ወንጀል ጥፋተኞች መባላቸውን ተከትሎ፣ ክሱን በሌለበት የሚሰማው አንደኛው ተከሳሽ ዘመነ ካሴ የቀረበበትን ክስ አጣጥሎታል። አንደኛ ተከሳሽ ዘመነ ካሴ “ኤርትራ ሄዶ የጦር ስልጠና ወስዶ መምጣቱን ፣ መንግስት አሸባሪ ብሎ ከሰየመው የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራሮች በተለይም ከጄኔራል ተፈራ ...

Read More »

ካርል ሃይንዝ ቦም አረፉ

ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦስትሪያዊው የፊል ተዋናይ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የ86 ዓመቱ ቦም ያረፉት በሚኖሩበት ሳልዝበርግ ከተማ ውስጥ ነው። ሰዎች ለሰዎች የተባለ የእርዳታ ድርጅት አቋቋመው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ሰብአዊ እርዳታዎችን ሲያደርጉ የቆዩት ቦም፣ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተወዳጅ ናቸው። ሰዎች ለሰዎች የተባለውድርጅት በአሁኑ ጊዜ በትዳር ጓደኛቸው ወ/ሮ አልማዝ ቦም እንደሚመራ ይታወቃል።

Read More »

በሊቢያ በርካታ አስከሬኖች ተገኙ

ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት በርካታ ስደተኞችን ጭና ከሊቢያ  ወደ ጣሊያን ስታምራ በሰጠመችው ጀልባ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች  ሳይሆን እንዳልቀረ የተገመተ አስከሬን  መገኘቱን የሊቢያ የአደጋ  መከላከ ሰራተኞችን በመጥቀስ ዓለማቀፍ  ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። የሊቢያ አደጋ መከላከል ሰራተኞች በጀልባዋ ከ150 በላይ ስደተኞች ተሳፍረው እንደነበር ለ አል ጀዚራ የገለጹ ሲሆን፤ እስካሁን  የተገኘው ግን የ 20 ዎቹ አስከሬንብቻ  ነው። አበዛኞቹ ተሳፋሪዎች ...

Read More »

የሃይማኖት ተቋማት ለብአዴን ጽህፈት ቤት ማሰሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ታዘዙ

ግንቦት ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀወት ወረዳ በሸዋ ሮቢት ከተማ ለሚገነባው የብአዴን ጽህፈት ቤት ማሰሪያ በወረዳዋ የሚገኙ ቤተክርስቲያኖች በነፍስ ወከፍ  1 ሺ 500 ብር እንዲከፍሉ በመታዘዛቸው፣ አስተዳዳሪዎቹ ገቢ ማድረጋቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። የሃይማኖት ተቋማት ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ እንደሆኑ ህግ ቢደነግግም፣ በተግባር የምናየው የዚህን ተቃራኒ ነው ያሉት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አስተዳዳሪዎች፣ ገንዘቡን ለጽህፈት ቤቱ ወስደው ያስረከቡት ከመንግስት የሚመጣውን በቀል ...

Read More »

ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከአገሯ አስወጣች

ግንቦት ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በካርቱም ሁዳ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት ከ800 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 40 እስረኞች ሰሞኑን ከእስር ቤት ወጥተው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ካርቱም አካባቢ የተሰበሰቡ  ከ600 በላይ ኢትዮጵያውያን ተጠርዘው ወደ አገራቸው መወሰዳቸውን እስካሁን ደረስ ኢትዮጵያ ይድረሱ አይደረሱ አልታወቀም። የሱዳን ፖሊስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ አዲስ በጀመረውን ኢትዮጵያውያንን ወደ ...

Read More »

የእሳት አደጋ መኪና አጠቃቀም የፈጠረው ውዝግብ ለከፍተኛ ንብረት መውድም መንስኤ እየሆነ ነው

ግንቦት ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ አስኮ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የአካል ጉዳተኞች መኖሪያ ቤት የሆነው ቲሻየር ሆም በተቃጠለበት ወቅት ነዋሪዎች ለአዲስ አበባ እሳት አደጋ መከላከያ መስሪያ ቤት የድረሱልን ጥሪ ቢያቀርቡም ፣ መስሪያ ቤቱ ግን የኦሮምያ ክልል ሳይፈቅድ መግባት አልችልም በሚል ምክንያት በተፈጠረው መዘግየት በቤቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ከመስሪያ ቤቱ ሰዎች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከዚህ ቀደም ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከ20 በላይ ነጋዴዎች ታሰሩ

ግንቦት ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊስ ራጉኤል አካባቢ የሚገኙ  በኮንትሮባንድ የገቡ የሞባይል ቀፎዎችን ይሸጣሉ ያላቸውን ነጋዴዎች ይዞ አስሯል። በድርጅቶቻቸው ውስጥ ያለውን ንብረት መውሰዱንም ነጋዴዎች ለኢሳት ገልጸዋል። አብዛኞቹ የሞባይል ቀፎዎች ከቻይና የመጡና በአብዛኛው አዲስ አበባ ክፍል አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የሚገልጹት የታሳሪ ነጋዴ ቤተሰቦች፣ እቃዎቹ ወደ አገር ውስጥ በኮንትሮባንድ ገብተዋል ከተባለም ከዋናው ከምንጩ ማደረቅ እንጅ እነሱ ተረክበው በሚያከፋፍሉት ላይ ...

Read More »

አብዱል ፋታህ አል ሲሲ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፋቸው ተሰማ

ግንቦት ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የግብጽ ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ሲሲ 93 በመቶ የሆነ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን የምርጫ ቆጠራ ውጤቶች አመልክተዋል። ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ከተጠበቀው ህዝብ መካከል 46 በመቶ የሚሆነው ብቻ ድምጽ መስጠቱ አል ሲሲ ከገመቱት በታች መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። አል ሲሲ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲን ከስልጣን በማውረዱ በኩል ከፍተኛ ስልጣን እንደነበራቸው ይታወቃል። የሙርሲ ደጋፊዎች ...

Read More »

ነዋሪዎች ግንቦት 20 ዳግም በኢትዮጵያ ሲከበር ማየት እንደማይሹ በምሬት ገለጹ

ግንቦት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው አንዳንድ ዜጎች ” የግንቦት20ን በአል ተገደው እንዲያከብሩ መደረጋቸውን ሲገልጹ” ፣ ሌሎች ደግሞ  በአሉ ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ምድር ተከብሮ ማየት እንደማይፈልጉ ገልጸዋል። ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ የግንቦት 20 ድል የመግብ ዋስትናችንን እንድናረጋግጥ እረድቶናል ያሉ ሲሆን፣ አገሪቱ በ1983 ዓም ታመርት ከነበረው 50 ሚሊዮን ኩንታል የግብርና ምርት ወደ 250 ሚሊዮን ኩንታል መሸጋገሩዋን ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም ይህን ይበሉ ...

Read More »

የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ታዋቂ ሰዎች የግንቦት 20ን በአልን በተመለከተ አስተያየቶችን ሰጡ

ግንቦት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የአንደኛው ክፍል ሊቀመንበር የሆኑት ጄል ከማል ገልቹ እንደተናገሩት የግንቦት20 በአል የኢትዮጵያ ህዝብ ከአንድ አስከፊና አንባገነን ስርአት ወደ አስከፊ፣ አንባገነንና ዘረኛ ስርአት የተሸጋገረበት ነው ብለዋል። ግንቦት20 ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ልምድና ምኞት አብሮ የማይሄድ ዘረኛ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረበት አሳዛኝ ቀን ነው ሲሉ አክለዋል የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትና የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ሊ/መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ...

Read More »