በኢትዮጵያ 34 ድርጅቶች ጤፍ ወደ ውጭ በመላክ ላይ ናቸው

ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የመንግስቱን የእርሻ ሰብል ድርጅት ጨምሮ 34 የንግድ ድርጅቶች ጤፍ ወደ ውጭ አገር በመላክ ላይ ናቸው። መንግስት በአገሪቱ የጤፍ ምርት እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ ጤፍ ወደ ውጭ እንዳይወጣ አግዶ የነበረ ሲሆን እገዳውን ከ ግንቦት ወር 2005 ጀምሮ  አንስቷል። አንድ ኩንታል ጤፍ በአዲስ አበባ ከ1800 እስከ 2000 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል።

Read More »

በእነማይ ወረዳ የመኢአድ አባላት እየተዋከቡ ነው።

ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምስራቅጎጃም ዞን  በነማይወረዳደንጎሊማቀበሌ የሚኖሩት አቶሞሳአዳነቅዳሜሰኔ 7 ቀን በኢህአዴግ ታጣቂዎች ከተገደሉ በሁዋላ ሌሎችም አባሎች እየተዋከቡ መሆኑን የወረዳው የመኢአድ ተወካይ መቶ አለቃ ደመላሽ ጌትነት ተናግረዋል። ግለሰቡ ገበያ ውሎ ሲመለስ አዲሱ ጫኔ እና ብርሃኑ ታምሩ የተባሉ ካድሬዎች መንገድ ላይ አስቁመው በዱላ ደብድበው እንደገደሉት የሟቹ ወገን የሆኑትና በህይወትና በሞት መካከል ባለ ጊዜ ደርሰው ቃሉን የተቀበሉት አቶ ይልቃል የሻነው ...

Read More »

ለመለስ ፋውንዴሽን ማሰሪያ እየተባለ በግዴታ የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈልገው በእጅጉ እንደሚልቅ ታወቀ

ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በሚል በአገሪቱ ያሉ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው በአማካኝ ከ17 እስከ 25 ሚሊዮን ብር ከህዝብ እንዲሰበስቡ ቢታዘዙም የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈለገው 300 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች ትርፉ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል። በአማራ ክልል  106 ወረዳዎች ያሉ ሲሆን ለፋውንዴሽኑ ማሰሪያ 2 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ይሰበሰባል። በኦሮምያ ደግሞ ከ205 ...

Read More »

የዋስትና መብት የተነፈጉ  ነጋዴዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃረር በቅርቡ ከተነሳው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ ከሚገኙት ከ20 በላይ ነጋዴዎችና ሰራተኞች መካከል ፍርድ ቤት የቀረቡት 3ቱ ተከሳሾች እንደገና ሌላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። የ25  አመቱ  ቢኒያም ጌታቸው፣ የ28 አመቱ ሲሳይ አሊ አህመድ እና የ16 አመቱ  ዙቤር  አህመድ  በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ በመተላለፍ ” በፌደራል ህገመንግስት የተቋቋመውን የሃረሪ ህዝብ ክልል መንግስት ፣ በዚህ ክልል ...

Read More »

ቻርለስ ቴለር ወደ አፍሪካ ሄደው የእስር ጊዜያቸውን እንዲፈጽሙ ጠየቁ

ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የላይቤሪያ መሪ ቻርለስ ቴለር በሴራሊዮን እኤአ ከ1991-2002 በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት እጃቸው አለበት በሚል በሄግ ኔዘርላንድስ በተቋቋመው ልዩ ፍርድ ቤት  የ50 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል። የእስር ጊዜያቸውን በእንግሊዝ የሚያሳልፉት ቴለር፣ 15 ልጆቻቸውን በየጊዜው ለማየት ባለመቻላቸው ወደ ሩዋንዳ ተወስደው እንዲታሰሩ ጥያቄ አቅርበዋል። ከቤተሰቦቻቸው እርቀው እንዲታሰሩ መደረጉ አለማቀፍ ህግን የሚጥስ መሆኑን የቴለር ጠበቆች ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ...

Read More »

በኦሮምያ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት መካከል አንዳንዶች ሲፈቱ ሌሎች ደግሞ ፍርድ አጥተው እየተሰቃዩ ነው

ሰኔ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮምያ ተነስቶ የነበረውን ተቃውሞ ተንተርሶ ከተያዙት በሺ ከሚቆጠሩ ወጣቶች መካከል የተወሰኑት ከእስር ሲለቀቁ፣ አብዛኞቹ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። የክልሉ ወኪላችን እንደሚለው በወለጋ፣  በአንቦና አጎራባች ወረዳዎች የታሰሩ በርካታ ወጣቶች አሁንም ፍትህ አጥተው በእስር ላይ ሲሆኑ በቡራዩ ታስረው ከነበሩት መካከል 3ቱ ዛሬ በዋስ ተለቀዋል። ጋዲሳ ጉደታ፣ ቱፋ በክሩ እና ጉዲሳ ...

Read More »

የሞያሌ ነዋሪዎች የደህንነት ክትትሉ እንዳስመረራቸው ገለጹው

ሰኔ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-2 የአልሸባብ አባላት ናቸው የተባሉ የሶማሊ ተወላጆች መያዛቸውን መንግስት ካስታወቀ በሁዋላ፣ በኢትዮጵያዋ የድንበር ከተማ ሞያሌ ከፍተኛ ጥበቃ እየተካሄ መሆኑንና በዚህም የተነሳ መንግስት በህዝቡ ላይ የሚያደርገው ክትትል እንዳስመረራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። መውጫ መግቢያ ማጣታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የደህንነት ሃይሎችና ታጣቂዎች ማታ ማታ በግለሰቦች ቤት ሳይቀር እየገቡ ፍተሻ ያካሂዳሉ ብለዋል። በምሽት ለመውጣት መቸገራቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ የአካባቢውን ...

Read More »

የአዳዲሶቹ የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ መጓተቱትን መረጃዎች አመለከቱ

ሰኔ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች ፕሮጀክቶችና የነባር የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች የግንባታ ስራዎች አፈጻጸም እጅግ ደካማ መሆኑን ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ጠቁሟል። ለዚህደካማአፈጻጸምሚኒስቴሩበዋንኛነት ያስቀመጠውምክንያትከስራውስፋትናውስብስብነትአንጻርያጋጠመውትልቅየማስፈጸምአቅምማነስነውብሏል፡፡በቀጣይዓመትበሚጠናቀቀውየመንግስትየዕድገትናየትራንስፎርሜሽንዕቅድየመጀመሪያዎቹሶስትዓመታትማለትምከ2003-2005 ኣ.ምየአዳዲስስኳርልማትፕሮጀክቶችየሚካሄዱትከዚህበፊትምንምየመሰረተልማትባልተዘረጋባቸውናለግንባታስራየሰለጠነየሰውኃይልበማይገኝባቸውአካባቢዎችበመሆኑበዕቅድዘመኑውስጥየመጀመሪያዎቹሁለትዓመታትማለትም 2003 እና 2004 የመንገድናሌሎችየአዋጪነትየጥናትስራዎችመከናወናቸውንመረጃውይጠቅሳል፡፡ በመሆኑምበእነዚህኣመታትለቀጣይስራመደላድልከመፍጠርባለፈተጠናቅቆ ወደምርትየገባፕሮጀክትአልነበረም፡፡ የነባርስኳርፋብሪካዎችየማስፋፊያፕሮጀክቶችየግንባታስራዎችመካከልየወንጂናየፊንጫስኳርፋብሪካዎችተጠናቅቀውበ2005 ኣ.ምወደስራየገቡሲሆንየተንዳሆስኳርፋብሪካበዚህዓመትወደስራእንደሚገባመረጃውይጠቅሳል፡፡ አዳዲሶቹስኳርፋብሪካዎችማለትምኩራዝ፣የጣናበለስእናወልቃትየመስኖመሰረተልማትግንባታ፣የመሬትዝግጅትናየሸንኮራአገዳተከላ፣የፋብሪካናየመኖሪያቤትግንባታዎችእየተከናወኑቢሆንምአፈጻጸማቸውበዝቅተኛደረጃላይእንደሚገኝተመልክቷል፡፡ በዚህምምክንያትፕሮጀክቶቹየዕድገትናየትራንስፎርሜሽንእቅዱ በሚጠናቀቅበትበቀጣይአንድኣመትጊዜያትእንደማይደርሱከወዲሁተረጋግጦአል፡፡ በአንድወቅትየስኳርኮርፖሬሽንዳይሬክተርየነበሩትአቶአባይጸሐዬየስኳርፋብሪካዎቹበዘርፉልምድ ባለመኖሩምክንያትየማስፈጸምአቅምማጋጠሙንአምነው  “እየተማርንበመስራትላይነን” በማለትበፓርላማመድረክያደረጉትንግግርበሃገርሐብትመቀለድነውበሚልከፍተኛትችትአስከትሎባቸውእንደነበርየሚታወስነው፡፡ በሌላ ዜና ደግሞ በውጭሃገርካሉኢትዮጵያዊያንእናመንግስታዊያልሆኑድርጅቶችአማካይነትወደ ሃገርውስጥየሚገባውሃዋላየወጪንግዱንገቢእየተገዳደረውመሆኑንከብሔራዊባንክየተገኘመረጃጠቆመ፡፡ እየተገባደደባለውየኢትዮጵያዊያን 2006 በጀትዓመትዘጠኝወራትከሸቀጦችኤክስፖርት 2  ቢሊየንዶላርሲገኝከግልሃዋላምተቀራራቢበሆነመልኩ 2 ቢሊየንዶላርተገኝቷል፡፡ አምናበ2005 በጀትዓመትሃገሪቱከሸቀጦችንግድ 3 ቢሊየንየአሜሪካንዶላርስታገኝከግልሃዋላደግሞ 4ቢሊየንዶላርማግኘትዋንመረጃውንይጠቅሳል፡፡ የባንኩመረጃእንደሚያሳየውበውጪአገርየሚኖሩኢትዮጵያዊንለወገኖቻቸውንናለተለያዩስራዎችማስኬጃወደሃገርውስጥየሚያስገቡትዶላርበዓመትእስከ 20 ...

Read More »

በኬንያ የሽብር ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ በርካታ ሰዎች ታሰሩ

ሰኔ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ እንደዘገበው በላሙ የወደብ ዳርቻ ሰሞኑን የተፈጸመው ጥቃት የ60 ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጥቃቱን የፈጸመው አልሸባብ አለመሆኑን ገልጸው ነበር። ጥቃቱ በአልሸባብ እንደተፈጸመ ተደርጎ መረጃውን ያሰራጨውን ሰው መያዙም ተገልጿል። ግድያው ከጎሳ ፖለቲካ ጋር የተያያዘ እንደሆነ የአገሪቱ መንግስት ገልጿል። ሰሞኑን በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 12 ሴቶችም ታፍነው ተወስደዋል። ታፍነው የተወሰዱት ሴቶች የት እንደገቡ ...

Read More »

የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉት ዜጎች ለክስ የሚያበቃ በደል አልደረሰባቸውም አለ።

ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት የመሰረቱት ክስ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃ ብሄር ምድብ በዋለው ችሎት የታየ ሲሆን ፣ በቀረበው ክስ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና የቤንሻንጉል ክልል መንግስት መልስ ሰጥተዋል። ከሳሾች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት ቀየ በህገወጥ መንገድ በመፈናቀላቸው ሃብትና ንብረታቸውን ማጣታቸውን በጠበቃቸው አማካኝነት ተናግረዋል። የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ ከሳሾቹ ቤት ንብረት ...

Read More »