መድረክ -ከገዥው ፓርቲ ጋር በአሰቸኳይ መወያዬተ እፈልጋለሁ አለ።

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች አሉኝ ያለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤    ከገዥው ፓርቲ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡ መድረክ በትናንትናው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች አመራረጥና በምርጫው ለሚሳተፉ ፓርቲዎች ከመንግስት በሚሰጠው የድጐማ ገንዘብ ክፍፍል ላይ ቅሬታ እንዳለው ተናግሯል። መድረክ አያይዞም፦”ምርጫውን ለማስፈፀምና ለመታዘብ ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ገለልተኛ የሆኑ ...

Read More »

ወደ ሰሜን ኢትዮጰያ ከባድ የጦር መሳሪያዎች እየተጓጓዙ ነው።

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት፤ ታህሳስ 26- 2007  ዓመተ ምህረት  ጧት እና ምሽት ላይ  በርካታ ታንኮችን እና ከባድ  ብረት ለበስ የጦር ተሽከርካሪዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጰያ አጓጉዟል። ከየት ቦታ እንደተነሱ ያልታወቁትና ወደ ሰሜን አቅጣጫ ያመሩት ታንኮች፤ ምሽት ላይ ወልዲያ ከተማ ማረፋቸውን  ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። መንግስት ከሰሜን አካባቢ ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ይችላል የሚል ግምገማ ማካሄዱን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።

Read More »

“አሜሪካ በየቀኑ እየቀጠቀጠን በመሆኑ ብንችል ቪኦኤን ድምጥማጡን እናጠፋው ነበር” ሲሉ የብአዴን ዋና ጻሃፊ ተናገሩ

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን ይህን የተናገሩት መጪውን ምርጫ አስመልክቶ ለተመረጡ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ለባለድርሻ አካላት ባደረጉት ገለጻ ነው። አቶ አለምነው ነጻ ሚዲያ በሌለበት አገር ኢሳትና ቪኦኤን የመሳሰሉ ነጻ ሚዲያዎችን ማፈን ተገቢ ነወይ የሚል የጽሁፍ ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን፣ ቪኦኤ በአሜሪካ መንግስት ሳንባ የሚተነፍስ ነው ፣  የአሜሪካ መንግስት  አላማ ደግሞ ...

Read More »

በድሬዳዋ አየር ሃይል ውጥረት የበዛበት ግምገማ ተካሄደ

ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራት ከፍተኛ ማእረግ ያላቸው የአየር ሃይል አብራሪዎች መጥፋታቸውን ተከትሎ በድሬዳዋ የአየር ሃይል ምድብ ሲካሄድ የነበረው የ3 ቀናት ግምገማ ሃሙስ እለት ተጠናቋል። በግምገማው ላይ አብራሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ ቴክኒሻኖችና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ ሰራተኞቹ ስለጠፉት አብሪዎች የተሰማቸውን ስሜት እንዲናገሩ፣ የሚያውቁትን ሚስጢር እንዲያወጡ ሲገደዱ ሰንብተዋል። ብዙዎች ” ስለጠፉት አብራሪዎች ምን ትላላለችሁ?’ እየተባሉ ሃሳባቸውን እንዲናገሩ የተጠየቁ ሲሆን፣ በሚሰጡት ...

Read More »

ምእራባዊያን ኢህአዴግን ከተቃዋሚዎች ጋር ለማቀራረብ ላይ ታች እያሉ ነው

ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ችግር እየከፋ መሄዱ ለህዝባዊ አመጽ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት ያደረባቸው ምእራባዊያን በአሜሪካ ፊት አውራሪነት በአገር ውስጥና በውጭ ያሉትን ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ጋር ለማቀራረብ እየተሯሯጡ መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ። እንደምንጮች ገለጻ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉት ድርጅቶች ውስጥ አንዳንዶችን በማካተት፣ በውጭ ከሚገኙ ገዢውን መንግስት በሃይል እናንበረክካለን ከሚሉ ወገኖች ጋር ለማቀራረብ ...

Read More »

ደርግ ከ 26 ኣመት በፊት  በትግራይ-በሀውዜን ላይ በፈጸመው ጭፍጨፋ የእስራ ዔል እጅ አለበት ሲሉ የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ተናገሩ።

ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው፣የቀድሞው የህወሀት ሊቀመንበር አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት የህወሀትን 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን ወደ ትግራይ ለተንቀሳቅቀሱት  ጎብኝዎች የደርግ 604ኛ ኮር የተደመሰሰበትን ወታደራዊ ሳይንስ አስመልክቶ  በሽሬ ከተማ በተሰናዳ መድረክ ላይ ባደረጉት ገለጻ ነው። “የቀዝቃዘውን ጦርነት ማክተም ተክትሎ ታላቋ ሶቪየት ህብረት መፈራረስ ጀመረች ያሉት አቶ ስብሀት፤ክስተቱን ተከትሎ ሲቪየት  ከኢትዮጵያ እየወጣች በመምጣቷ ...

Read More »

የተቃዋሚ መሪዎች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 6 የተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮችና ሌሎች ዜጎች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ሁለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሰጠባቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽ ...

Read More »

በጋምቤላ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት 79 ሰዎች  መገላቸውን መንግስት ገለጸ

ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በጋምቤላ ክልል በጎደሬ ወረዳ ከመጋቢት እስከ ጳጉሜ በነበሩት ግጭቶች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ12 አይበልጥም በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቢቆይም፣ አቃቢ ህግ የክልሉን ባለስልጣናት ለመክሰስ ባቀረበው የክስ ቻርጅ ላይ 79 ሰዎች መገደላቸውን ፣ 273 ቤቶች መቃጠላቸውን ከ13 ሺ በላይ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸውን ገልጿል። አንዳንድ ወገኖች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር በመቶዎች እንደሚቆጠሩ ሲገልጹ፣ ኢሳት ...

Read More »

የእስቴ መምህራን ተቃውሞ አሰሙ

ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር እስቴ ወረዳ የሚገኙ  መምህራን ለ3 ቀናት የሚቆይ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስብሰባ እንዲካፈሉ ቢጠሩም፣ መምህራኑ በስብሰባው ላይ ከተገኙ በሁዋላ፣ በአንድ ድምጽ ስብሰባ ኣንሳተፍም በማለት ጥለው ወጥተዋል። መምህራኑ መንገድ የመሳሰሉ የመሰረተ-ልማቶች አልተሟሉም፣ ለመምህራን በቂ የሆነ ክፍያ አይሰጥም በማለት ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የተጠራው ስብሰባ በተቃውሞ ታጅቦ መበተኑንና የመምህራኑ  ያለተጠበቀ ...

Read More »

24 ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ሲያቀኑ ባህር ላይ ሰጠሙ

ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን አገር ውስጥ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያውያኑ  ሞቻ በሚባለው የወደብ ከተማ አቅራቢያ  ሲደርሱ የተሳፈሩበት ጀልባ በመስጠሙ 24ቱም አትዮጵያውያን አልቀዋል። የሁሉም አስከሬን መገኙቱን ባለስልጣኑ ሲናገሩ፣ የተረፉ ካሉም በማፈላለግ ላይ መሆኑን አስታውቋል። ባለፈው ወር ከ79 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ባህር ላይ ማለቃቸው ሲታወስ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባህር ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር 100 አድርሶታል። ስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው ...

Read More »