የታዋቂው የሬጌ አቀንቃኝ የቦብ ማርሌይ ሐውልት በአዲስ አበባ ሊቆም ነው።

ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሐውልቱ  ስራ  አስተባባሪዎች መካከል  የጃኖ  ባንድ መስራች የሆነው አርቲስት አዲስ ገሰሰ  ለታዲያስ  አዲስ እንደገለጸው፤  የቦብ  ማርሌይ  ሐውልት  ከሶስት  ሳምንት  በሁዋላ  በገርጂ  ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ይቆማል። በምርጫ 97 ዋዜማ የቦብ ማርለይ 60ኛ አመት በመስቀል አደባባይ  ሲከበር፤ በወቅቱ  የመዲናዋ  ከንቲባ  የነበሩት አቶ አርከበ  እቁባይ  በበአሉ የተገኙትን የቦብ ማርለይ ቤተሰቦችን ሐውልቱ ይቆምበታል ወደተባለው ...

Read More »

<<ዝም ብላችሁ ጥሩ ነገር ብቻ ብትናገሩ አንሰማችሁም፤ እንደውም አጭበርባሪ ነው የምንላችሁ>> ሲሉ  ዶክተር ደብረጽዮን  ገብረሚካኤል -አርቲስቶችን ተናገሩ።

ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ደብረጽዮን- ከአርቲስቶች ጋር  ባደረጉት ዝግ ስበሰባ የተናገሩት ነገር ተቀርጾ  በይፋ  በማህበራዊ  ሚዲያዎች የተለቀቀ ሲሆን፤ በንግግራቸው አርቲስቶችን ሲመክሩና፣ ሲያባብሉ እና  ሲገስጹ ተሰምተዋል። <<በፌስ ቡክ የሚነገረንን ነገር እንሰማለን፤አርቲስቶች ሆዳሞች እንደምትባሉ እናውቃለን!>> ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፤ <<መለስን ሳይቀር የሚሳደቡ አሉ፤ መለስን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ሲሰድቡን አይተናል>> ብለዋል። <<እናንተም  የፈለጋችሁትን ነገር ንገሩን፤ ...

Read More »

 ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ   በዮሐንስ እጅ መጠመቁን ምክንያት በማድረግ በመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ዘንድ  በየኣመቱ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ዘንድሮ  በመላ ሀገሪቱ በድምቀት ተከብሯል።

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር በፋሲል ግንብ አጠገብ በተከበረው በዓለ-ጥምቀት ከትናን የከተራ እለት ጀምሮ በርካታ ቱሪስቶች መገኝታቸውን ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል። በዓሉ በአዲሰ አበባ ጃን ሜዳም – እንደ ወትሮው ሁሉ እጅግ በደመቀ ሁኔታ መከበሩ ታውቋል። በላሊበላ እጅግ በርካታ ቀሳውስት ተገኝተው በወረብና በዝማሬ ማክበራቸውንም በስፍራው ያለችው ወኪላችን የላከችው መረጃ ያመለክታል። እንዲሁም በተለያዩ የውጪ ሀገራት የሚገኚ  የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች  ...

Read More »

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ  ከስድስት ወራት በሁዋላ  ለመጀመሪያ ጊዜ ልጆቻቸውን ጨምሮ ከቤተሰቦቻቸው ጋር  በስልክ መነጋረራቸው ተስፋ እንደሰጣቸው ባለቤታቸው ወይዘሮ የምስራች ገለጹ።

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወይዘሮ የምስራች በተለይ ለኢሳት  ሲናገሩ፤ አቶ አንዳርጋቸው ካልታወቀ እስር ቤት ሆነው ልጆቻቸውንና የቤተሰቡን አባላት ድንገት ሲያናግሩ ደንግጠው እንደነበር በመጥቀስ፤ ድንገት የተደወለውን ስልክ ሲያነሱ በድምጻቸው ወዲያው እንደለዩዋቸው ግልጸዋል። ሰላምታ ከተለዋወጡ በሁዋላ ጤንነታቸውን በተመለከተ እንደተጠያየቁና   አቶ አንዳርጋቸው በደህና ጤንነት ላይ መሆናቸውን እንደገለጹላቸውም ወዘይሮ የምስራች ተናግረዋል። <<ድምጹን ሥንሰማው  ደስታም፣ድንጋጤም የተቀላቀለበት ፤ እንዲሁም ምንም ልናደርግለት ...

Read More »

በባህር ዳር ሲካሄድ የነበረው የመምህራን ስልጠና ያለስምምነት ተጠናቀቀ፤መንግስት ስልጣኑን እንዲያስረክብ ተጠየቀ።

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህር ዳር ከተማ  ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች  መምህራን ሲካሄድ የቆየው ስብሰባ የታሰበለትን ዓላማ ሳያሳካ መጠናቀቁን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ያጠናቀረው መረጃ ያመለክታል። መንግስት  ሰሞኑን ትምህርት ቤቶችን ለአንድ ሳምንት በመዝጋት ለግልና ለመንግስት መምህራን ሲሰጠው የቆየው ስልጠና በሚጠናቀቅበት ጊዜ መምህራን  በተሰጡት በሁሉም ርዕሶች ላይ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ስልጠናው መጠናቀቁን በስብሰባው የተሳተፉ ...

Read More »

በተቃዋሚዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል ተባብሶ ቀጥሏል

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) አስተባባሪ  የሆነው ወጣት ዘመነ ምረተአብ ትናንት ጥር 10 ቀን  11:00  አካባቢ  በማክሰኝት ከከተራ በዓል ላይ ባልታወቁ ሰዎች ተወስዷል። አፋኞቹ ዘመነ ምረተአብን ወዴት እንደወሰዱትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እስካሁን አልታወቀም። ቀደም ሲል የታሰሩት  የመኢአድ የቀድሞ  ዋና ጸሃፊ አቶ ተስፋየ ታሪኩ፣ የድርጅቱ የደቡብ ጎንደር ዋና ጸሃፊ የሆነው ...

Read More »

መንግስት በካራቱሪ ኩባንያ እምነት  ማጣቱን ገለጸ

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካራቱሪ በበኩሉ መንግስት አስፈላጊውን ነገር አላመቻቸልኝም ባይ ነው። የህንዱ ግዙፍ ኩባንያ <<ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ>> በኢትዮጵያ ሲያደርግ በቆየው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መንግሥት እምነት እንዳጣበት መግለጹን ሪፖርተር ዘግቧል። አቶ አበራ ሙላት ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኩባንያው ይጠበቅበት የነበረውን ሥራ ማከናወን ሳይችል ቀርቷል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ...

Read More »

የአማራ ክልል ፖሊሶች  ከመቼውም በበለጠ  እርምጃ ለመውሰድ በተጠንቀቅ እንዲሆኑ ተነገራቸው

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሶቹ በበኩላቸው – <<እኛን ህዝብ ጋር አታጣሉን>> ሲሉ ለአዛዦቻቸው ትእዛዝ ምላሽ ሰጥተዋል። የክልሎ ፖሊሶች  ከመቼውም በላይ ለእርምጃ እረንዲዘጋጁ  የተነገራቸው፤የማረሚያ ቤቶችንና የትራፊክ ፖሊሶችን ጨምሮ ላለፉት ስድስት ቀናት በአማራ ክልል ለሚገኙ ፖሊሶች በሚሉ ሲሰጥ በነበረው ስልጠና  ላይ ነው። እስከ ትናንት ሐሙስ  ድረስ በቆየው በዚሁ ስልጠና ላይ ከምርጫው  እና ከጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ ሁኔታ ሊፈጠሩ የሚችሉ ...

Read More »

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም በወታደሮች ተደበደበ

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዝዋይ ወህኒ ቤት የሚገኘውን ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ትናንት ማለዳ ወህኒ ቤቱ በራፍ ላይ የደረሰው ታሪኩ ደሳለኝ በወህኒ ቤቱ ሀላፊና ስምንት በሚደርሱ ወታደሮች ድብደባ እንደደረሰበት በፌስ ቡክ ገጹ ታሪኩ አስታውቋል፡፡ለተመስገን ይዞ የመጣውን ምግብ ወታደሮቹ መሬት ላይ ከመድፋታቸውም በላይ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ ወስደውበታል፡፡ታሪኩ ከደረሰበት ድብደባ በላይ ወንድሙን ሳይጠይቅና የሚገኝበትን ሁኔታ ሳያጣራ መመለሱ ህመም ...

Read More »

ገዥው ፓርቲ መጪውን ምርጫ ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን በህዝቡ ላይ ጭምር ከፍተኛ ጫና እየፈጸመ እንደሆነ በተለያዩ ክልል ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ።

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ፣የደሴ፣ የሀዋሳ፣የአርባምንጪ፣ የሀረር፣ የሚዛን ተፈሪ፣የሰበታ፣ የባህርዳር፣ የወልቂጤና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች  ለኢሳት እንደገለጹት፣በካድሬዎች አማካይነት ህዝቡ የምርጫ ካርድ በግዳጅ እንዲወስድ እና ድምጹን ለኢህአዴግ እንዲሰጥ እየተደረገበት ያለው ግፊት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከፋ መጥቷል። ከካድሬዎቹ ማስፈራሪያዎች መካከል፦<<የምርጫ ካርድ ካልወሰዳችሁ የቀበሌ መታወቂያና ሌሎችንም አስተዳደራዊ አገልግሎቶች አታገኙም፣ በምርጫው ኢህአዴግን ካልመረጣችሁ ሁዋላ ላይ ተጣርቶ እርምጃ ይወሰድባችሁዋል፤የትም የማይደርሱ ተቃዋሚዎችን እንመርጣለን ...

Read More »