በሱዳናዊው የመኪና አሽከርካሪ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያዊት አረፈች

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካቲት 24 ፣ 2007 ዓም በሱዳናዊ ሹፌር በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት የተፈጸመባት ኢትዮጵያዊት ወጣት ማረፉዋን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወጣቷ በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ተወጋግታ መሞቱዋን የገለጹት የወረታ ነዋሪዎች፣ ሹፌሩ በቁጥጥር ስር ውሎአል ቢባልም በትክክል ስላለበት ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ጭኖ ይጓዝ የነበረውን መኪና ሹፌር ወደ ባህርዳር እንዲወስዳት  እንፍራንዝ ...

Read More »

ከፍተኛ  የመንግስት  ባለስልጣናት  አበል ካልተሰጠን ፍርድ ቤት አንቀርብም አሉ

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከሳሽ ኣቃቤ  እና  ህግ በተከሳሽ አቶ ኣስገደ ገ/ሥላሴ መካከል ሲደረግ በነበረው ክርክር  ለምስክርነት የተጠሩት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊቀርቡ ባለመቻካቸው  በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ  ቢታዘዝም፤  ባለስልጣናቱ  ከለመዱት ምቹ ህይወት አኳያ ማቅረብ ሳይቻል ቀረ። የህወሀት የደህንነት ሰራተኛው ብስራት አማረ  የመሰረተባቸውን ክስ  ተከትሎ ላለፉት ሶስት ዓመታት ሲከራከሩ  የቆዩት የቀድሞው የህወሀት ታጋይና የአሁኑ የሰማያዊ ፓርቲ አባል አቶ ...

Read More »

በጄኔቫ የሚገኘው የኢትዮጰያ ኤምባሲ  “የተቃዋሚ ደጋፊዎች ናችሁ”ላላቸው ኢትዮጰያውያን ፓስፖርት አላድስም አለ።

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊዘርላንድ የዙሪክ ነዋሪ የሆኑት አክቲቪስት  ፊዮሬላ ሮማኖ ለኢሳት እንደገለጹት  ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ቀጠሮ አስይዘው ከሚኖሩበት ዙሪክ ኤምባሲው ወደሚገኝበት ጀኔቫ የ3 ሰዓት መንገድ ተጉዘው ቢሄዱም፣ የኤምባሲ ስራተኞቹ በአካል ሲያዩዋቸው በተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደሚሳተፉ ስለለዩዋቸው አገልግሎቱን  ሳይሰጡ መልሰዋቸዋል። ኤምባሲው እንደደረሱ ጎይቶም በሚባል ሰራተኛ የተሰጣቸውን ፎርም ከሞሉና ፎቶግራቸውን ከሰጡ በሁዋላ በስዊዘርላንድ ለምን ያህል ዓመት እንደቆዩ ጥያቄ የቀረበላቸው ...

Read More »

ካህኑ የአረና አባል በመሆናቸው ዘግናኝ ድብደባ ተፈጸመባቸው

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀፍታ ሑመራ ወረዳ  በረኸት  ከተማ  ነዋሪ የሆኑት ቄስ ሕሉፍ ኸሕሳይ የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ዘግናኝ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከፓርቲው ጽህፈት ቤት የወጣ መረጃ አመለከተ። እንደ መረጃው ከሆነ  ቄስ ህሉፍ  በደረሰባቸው ዘግናኝ ድብደባ  በህይወትና በሞት መካከል የሚገኙ ሲሆን፤ ለድብኢደባቸው ምክንያቱ  የአረና አባል መሆናቸው ብቻ ነው። የካቲት 17 ቀን 2007ዓመተ ምህረት  ምሽት 1፡00 ሰዓት ኣከባቢ  ...

Read More »

አንድ ሱዳናዊ ሹፌር ኢትዮጵያዊቷን በጩቤ ወግቶ ከመኪና ላይ መወርወሩ ህዝባዊ ቁጣ አስነሳ

የካቲት ፳፬(ሃያአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጊቱ የተፈጸመው  ማክሰኞ የካቲት 24 ፣ 2007 ዓም ሲሆን አንድ የሱዳን ታርጋ ያለው ፣ በሱዳናዊ ሹፌር የሚሽከረከር ማዳበሪያ ያጫነ ከባድ መኪና  ከሱዳን ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ ነው። መኪናው እንፍራዝ እየተበላ በሚጠራ አነስተኛ ከተማ ላይ ሲደርስ አንዲት መኪና በመጠበቅ ላይ የነበረች ኢትዮጵያዊት ወጣት ሹፌሩን ትብብር ጠይቃው  ትሳፈራለች።  ምክንያቱ በውል ባይታወቅም፣ አንዳንዶች እንደሚሉት ሊደፍራት በመሞከሩና ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልእክቱን እንዲለውጥ ተጠየቀ

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ፣ ኤፍ ኤም 96.3፣ ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫ ቅስቀሳ ያቀረባቸውን መልእክቶች እንዲለውጥ፣ ካልለወጠ ግን እንደማያስተላልፍ ገለጸ። ጣቢያው እንዲወጡ ከጠየቃቸው መልእክቶች መካከል ‹‹ሀገራችን ዛሬ በቀሪው ዓለም የምትታወቀው በእርስ በርስ ጦርነት ነው›› የሚለው የሚገኝበት ሲሆን፣ መልእክቱ ለአመጽና ለሁከት የሚያጋልጥ ነው የሚል ምክንያት አቅርቧል። ሌላው እንዲወጣ የተጠየቀው ‹‹ህዝቧ ...

Read More »

በቀድሞ መንግስት ምርኮኛ ወታደሮች የተመሰረተው ኦህዴድ የ25 ዓመት የምስረታ በዓሉን ሊያከብር ነው

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞ የደርግ ወታደሮችን በማሰባሰብ  በህወሓት በጎ ፈቃድ የተመሰረተው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የተመሠረተበትን 25 ዓመት በድምቀት ለማክበር መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳባ ደበሌ  በሰጡት መግለጫ ኦህዴድ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል ከመጋቢት 1 እሰከ መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በልዩ ልዩ መርሃግብሮች ያከብራል፡፡ በወጣው ፕሮግራም መሰረትም ከመጋቢት ...

Read More »

ም/ል ጠ/ሚኒስትሩ ተቃውሞ ገጠማቸው

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅዱስ ጊዮርጊስ እና  የአልጀሪያው -ኤል ኡልማ  ቡድኖችን  ጨዋታ ለማየት በባህርዳር ስታዲየም በእንግድነት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ከጨዋታው በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ሰአት ጨዋታውን ለመመልከት በስቴዲየሙ የተገኘው ሕዝብ በታላቅ ቁጣ የተቃውሞ ድምጽ በማሰማቱ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን የክልሉ ወኪላችን ገልጻለች፡፡ አብዛኛው ህዝብ ከተቃውሞ ድምጹ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት በእጁ በማሳየት አቶ ደመቀ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ ...

Read More »

የአድዋ ድል በአል ተከበረ

የካቲት ፳፫(ሃያሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን የጣሊያንን ወራሪ ሃይል ድል የመቱበትና ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁሮች በነጮች ላይ የአሸናፊነት ታሪክ የጻፉበት የአድዋ ድል 119 አመት በአል በአዲስ አበባ ተከብሮአል። በርካታ አርበኞችና ወጣቶች ፣ የአድዋን ድል በመሩት በአጼ ሚኒሊክ ሃውልት ዙሪያ በመሰባሰብ ቀኑን አክበረው የዋሉ ሲሆን ወጣቶች  የጀግንነት መገለጫ የሆነውን ባህላዊ ሽለላ ሲያሰሙ፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ በፖሊስ እንዲበተኑ ተደርጓል። ፖሊሶች ያልተፈቀደ ሰልፍ ...

Read More »

የብረታብረት ኢንዱስትሪዎች ለኪሳራ መዳረጋቸው ተገለጸ

የካቲት ፳፫(ሃያሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብረታብረት ኢንዱስትሪዎች  ከኃይል አቅርቦት መቆራረጥ፣ ከአቅርቦት ማነስ እንዲሁም ከውጪ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተያይዞ በሙሉ አቅማቸው ማምረት አለመቻላቸውና ለኪሳራም እየተዳረጉ መሆናቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ የብረታብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ሰሞኑን በግዮን ሆቴል የ2007 ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ባሳወቀበት ወቅት እንደተጠቀሰው በብረታበረት ዘርፍ ወደ 60 የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ኢንዱስትሪዎች በዋንኛነት ከኃይል አቅርቦት ...

Read More »