ከ2 አመት በፊት ከቴሌ የተባረሩ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰራተኞች በቴሌ በሚወጡ ስራዎችን ላይ ተወዳድረው እንዳይቀጠሩ እንደተከለከሉ ተናገሩ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮፕያ ቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የቴሌኮሚኒኬሽን ውል፤ ዜድ ቲ ኢ እና ሁዌይ ለተሰኙ ሁለት የቻይና ኩባንያዎች እንደሰጠ የታወቀ ሲሆን፤ ከ2 አመት በፊት ከቴሌ የተባረሩ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ደግሞ በችግር ከመሰቃየታቸውም በላይ፤ በቴሌ የሚወጡ ስራዎችን ተወዳድረው እንዳይቀጠሩ እንደተከለከሉ ተናገሩ። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚ/ሩ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በአሜሪካን ኮንግረስ በስለላና የአሜሪካንን ቴክኖሎጂ ሰርቆ ለቻይና በመስጠት ...

Read More »

የኢኮኖሚ እድገቱ በምርታማነትና በኢትዮጵያ ሀብት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፤ በአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ በኩል እንደሆነ ተገለጸ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- መንግስት የአገሪቱ ኢኮኖሚ ለ10ኛ አመት በድርብ ቁጥር ያድጋል ቢልም፤ የኢኮኖሚ እድገቱ በምርታማነትና በኢትዮጵያ ሀብት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፤ በአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ በኩል እንደሆነ ተገለጸ “ዚስ ኢዝ አፈሪካ” የተሰኘው የተሰኘው ድረገጽ እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዓለም ላይ በፍጥነት ከሚያድጉት አምስት ኢኮኖሚዎች ውስጥ ነው ቢባልም፤ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት፤ የቴክኖሎጂ ዘርፍና፤ የባንኩ ዘርፍ በጣም  ሁዋላቀርና በአፍሪካ ደረጃ እንኩዋን ...

Read More »

በዛሬው የጁመዓ ጸሎት ሙስሊሞች በዝምታ ተቃውሞአቸውን አካሂደው በሰላም ተበትነዋል

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው የጁመዓ ጸሎት የስግደት መርሀ ግብር ላይ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአዲስ አበባ መርካቶ አንዋር መስጊድ በዝምታ ተቃውሞአቸውን አካሂደው በሰላም ተበትነዋል ዛሬ ከቀኑ 4፡30 ጀምሮ በአንዋር መስጊድ እና በአካባቢው ከፍተና ቁጥር ያላቸው የመንግስት የደህንነት ሀይሎች በአለባበስ ሙስሊም መስለው መቀላቀላቸውን ለዘጋቢአችን የገለጡት አንድ የመስጊድ አስተናጋጅ፣ የፌደራል ፖሊሶች ዝግጁ ሆነው በኡመር ሰመተር ትምህርት ቤት እና በአራተኛ ፖሊስ ...

Read More »

የ 1 ዶላር ምንዛሬ ለማግኘት 1 ብር ከ 25 ሳንቲም ጉቦ መክፈል ግድ ነው ተባለ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከወጋገን ባንክ በስተቀር በአብዛኞቹ የአገሪቱ ባንኮች የውጪ ምንዛሬ በመጥፋቱ፤  ምንዛሬ ፈላጊዎች  በእያንዳንዷ ዶላር  1 ብር ከ 25 ሳንቲም ጉቦ  እንዲከፍሉ መገደዳቸው  ተዘገበ።   በዚህም መሰረት አንድ ሰው የአንድ መቶ ሺ ዶላር ምንዛሪን ለማግኘት፤  ለምናዛሬ ፈቃጅ አካላቱ እስከ 125 ሺ ብር  ጉቦ መክፈል ግዴታው ሆኗል።   በቅርቡ የተከሰተውን የውጪ ምንዛሬ እጥረት በመጠቀም የአንዳንድ ባንክ ...

Read More »

ስዊድናዊያኑ ያሰባሰቡትን ገንዘብ ለእስረኞች ሊለግሱ ነው

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሽብርተኝነትን በመርዳት ክስ ተመስርቶባቸው ላለፈው አንድ ዓመት በ ኢትዮጵያ ከታሰሩ በሁዋላ በቅርቡ በይቅርታ የተለቀቁት ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች በሽልማት ያገኙትን 10 ሺህ የስዊድን ክሮነር በቃሊቲ እስር ቤት በዞን ስድስት ውስጥ ላሉ እስረኞች ለማበርከት ወሰኑ። በ እስር ቆይታቸው የኢትዮጵያውያንን አብሮ የመብላት ባህል ማየታቸውን የገለፁት  ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፔርሰን፤ 10 ሺህ ክሩነሩን የለገሱት፤ የኢትዮጵያ ዓመት ...

Read More »

በአሜሪካ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ምርመራ የሚደረግባቸው የቻይና የቴሌኮሚኒኬሽን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛውን ድራሻ ይዘው በመስራት ላይ ናቸው ነው ተባለ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ  ኮንግረስ ፓናል ሁአዌይ እና ዜድ ቲኢ የተባሉት የቻይና የቴሌኮሚኒኬሽን ኩባንያዎች የሚጠቀሙባቸው የስለላ መሳሪያዎች ለአሜሪካ ደህንነት አስጊ በመሆናቸው መንግስት ልዩ ክትትል እንዲያደርግባቸው መጠየቁ፣ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ከሳበ በሁዋላ እነዚህ ሁለት ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ውስጥ ታላቅ ድርሻ እንዳላቸውና በሚቀጥሉት 2 አመታትም ከፍተኛ ስራ ለመስራት መዘጋጀታቸው ታውቋል። ዜቲኢ ኩባንያ ለኢትዮጵያ መንግስት የሞባይል ቴክኖሎጂን በማስፋፋት ...

Read More »

በዳኞች ሹመት የብሔር ተዋጽዖ ጉዳይ አከራከረ

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጽያ ፓርላማ ዛሬ መደበኛ ስበሰባውን ባካሄደበት ሥነሥርዓት ከዳኞች ሹመት ጋር ተያይዞ የብሔር ተዋጽኦ እና የብሔር ማንነት ጉዳይ በኢህአዴግ 99 በመቶ የተያዘውን ፓርላማ አከራከረ፡፡ ፓርላማው አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ የላኩትን የዳኞች ሹመት  ጉዳይ ላይ በተወያየበት ወቅት አባላቱ ባላተለመደ መልኩ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የዳኞቹ የብሔር ተዋጽዖ ምን ያህል የተጠበቀ ነው ከሚል ጀምሮ ታዳጊዎቹ ...

Read More »

የህወሀት ኩባንያ የሆነው ሱር ኮንስትራክሽን ገቢው በእጥፍ መጨመሩን አስታወቀ

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያን ሀርነት ትግራይ ንብረት የሆነውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን በዋና ስራ አስኪያጅነት የሚመሩት  ሱር ኮንስትራክሽን አመታዊ ገቢውን ከ1 ቢሊዮን 3 ሚሊዮን ወደ 2 ቢሊዮን 3 መቶ ሚሊዮን አሳድጓል። ሱር ኮንስትራክሽን እየተባለ የሚጠራው የህወሀት ኩባንያ ባለፈው አመት 203 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ይህም አሀዝ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ማደጉን ብሉምበርግ ዘግቧል። ሱር በመንግስት ቁጥጥር ስር ...

Read More »

አቶ አየለ ጫሚሶ በሕገወጥ ዶላር ምንዛሪ ለመጠቀም ሞክረው ባለመሳካቱ ግብረአበሮቻቸውን በወንጀል ከሰሱ

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሕጋዊ ወራሸ እኔ ነኝ የሚሉት አቶ አየለ ጫሚሶ ፎርጅድ ገንዘብ በማዘዋወር ወንጀል ውስጥ ተሳትፈው በተፈጠረ አለመግባባት ጉዳዩን ወደፖሊስ ወስደው ራሳቸው ነጻ የሆኑበት የሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር የወንጀል ድርጊትን አንዳንድ የፖሊስ አባላት ተቃወሙት ፡፡ አቶ አየለ ጫሚሶ ኦልበሞ መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ  ቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ...

Read More »

ኢትዮጵያ ባለፈው የበጀት አመት ከ47 ቢሊዮን ብር በላይ በእርዳታና በብድር መልክ ማግኘቷ ታወቀ

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፈው የበጀት አመት አገሪቱ በእርዳታና በብድር መልክ 47 ቢሊዮን ብር ወይም ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ አግኝታለች። ከዚህ ውስጥ 28 ቢሊዮን ብር በእርዳታ መልክ ቀሪው ደግሞ በብድር መልክ የተገኘ ነው። ባለፈው አመትም አገሪቱ ካለባት እዳ ውሰጥ  324 ሚሊዮን ብር እንደተሰረዘላት ታውቋል። የኢትዮጵያ መንግስት አገሪቱ ያለባትን እዳ በትክክት ለህዝብ ግልጽ ...

Read More »