በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ዘለፋ አዘል ግምገማ ተካሄደ

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት  ኢህአዴግ፣  ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው ተገምጋሚ ራሳቸው ሆነዋል። በጠ/ሚኒስትር አቶ ...

Read More »

የዜጎች መታፈን ተባብሶ ቀጥሎአል

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ አገዛዙን ይቃወሙ ይሆናል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በገፍ እየተያዙ በመታሰር ላይ ሲሆኑ፣ በርካታ ወጣቶችም ከእስር ለማምለጥ መሸሸጋቸውን ለኢሳት እየገለጹ ነው። በተለያዩ ክልሎች የገዢው ፓርቲ አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ ወጣቶች የሚታሰሩት ከምርጫው ጋር በተያያዘ ህዝቡን ለአመጽ ያነሳሳሉ በሚል ነው። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መሪ የነበሩት አቶ ማሙሸት አማረ   ዛሬ ...

Read More »

ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በመጨረሻው የኢህአዴግ ዙር ግምገማ መተቸታቸው

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችንና የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በሙሉ ሲያስገመግሙ ከከረሙ በሁዋላ በመጨረሻ ራሳቸው 15 ሰአታት በፈጀ ግምገማ ተገምግመዋል። አብዛኞቹ በአቶ ሃይለማርያም የስራ ችሎታና አመራር ላይ ዘለፋ ቀረሽ ሂስ አቅርበውባቸዋል። አቶ ሃይለማሪያም የቀረበባቸውን ሂስ ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸው ግምገማው ረጅም ጊዜ እንዲወስድ አድርጓል። ግምገማው ከምርጫው በሁዋላ የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ ባለስልጣናትን ለመለየት እና ግድፈታቸውን አርመው ሰርተው እንዲጠብቁ ...

Read More »

ሰመጉ በሃመር ወረዳ የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ ያጣራውን ሪፖርት ይፋ አደረገ

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)፣ በደቡብ ኦሞ ዞን በሐመር ወረዳ ዲመካ ከተማና አካባቢው ከጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተ ግጭት በ7 ሰዎች የሞትና በ9 ሰዎች የመቁሰል አደጋ መድረሱን በጥናቱ አረጋግጧል። ሰመጉ ባለሙያዎቹን በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከተማ እንዲገኙ በማድረግ የግጭቱን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት ዓይነትና ...

Read More »

ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አዋሽ አርባ በሚባል ቦታ መታሰራቸው ታወቀ

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ሳምንታት በውዴታና በግዴታ ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡ  ወጣቶች አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መታሰራቸውን አምለጠው የመጡ ወጣቶች ለኢሳት ተናግረዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ወጣት “በመጀመሪያ የወረዳው ባለስልጣናት ለስብሰባ ጠርተውን መንጃ ፈቃድና ልዩ ልዩ ስልጠና ስለምንሰጥ ከነገ ጀምሮ ተነሱ አሉን። እኔና 50 የምንሆን ጓደኞቼ በማግስቱ አዋሽ አርባ በሚባል ቦታ ተወሰድን። ...

Read More »

በታሰሩ የፌደራል ፖሊስ ስልኮች ላይ የተገኙት የአቶ አንዳርጋቸውና የመንግስቱ ሃይለማርያም ፎቶዎች መሆናቸው ታወቀ

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በተወሰኑ የፊደራል ፖሊስ አባላትና እና በማረሚያ ቤቶች ጠባቂዎች ላይ በተካሄደ ድንገተኛ ማጣራት፣ በ18 የፀጥታ አባላት ስልኮች ላይ በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም  ፎቶዎች መገኝታቸውን የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል። የደህንነት ሃይሉ ከባለቤቱ ፈቃድ ውጭ ስልክ የመጥለፍ ፤ የኢንተርኔት አካውንት በመስበር መረጃ የመስረቅና መረጃ የማዛባት ፣ ...

Read More »

ለመብራት መቆራረጡ ሰራተኞች ተጣያቂ ተደረጉ

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ ሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ መብራት እየተቆራረጠ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በህዝቡ ጥያቄ የተወጠሩት የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት  ሃላፊ ሠራተኞቻቸውን ተጠያቂ አድርገዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት  የውጭ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ገብረእግዚአብሔር ታፈረ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ለመብራት መቆራረጥ መንስኤ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ ምግባረ ብልሹ ሠራተኞቻቸው መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል። ሃላፊው ተቋሙ ከ13 ሺ ...

Read More »

በጋምቤላ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት  ሰዎች ተገደሉ

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላ እና በደቡብ ክልል አዋሳኝ ከተሞች የሚታየው የጸጥታ ሁኔታ እየተበላሸ መሄዱን ተከትሎ  ዜጎች እየተፈናቀሉና እየተገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከሁለት ቀን በፊት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በጎደሬ ወረዳ በየሪ ቀበሌ በፈጸሙት ጥቃት 6 ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሰው ደግሞ በጽኑ ቆስሎ ሆስፒታል ገብቷል። ሌሎች ወገኖች ደግሞ የማቾች ቁጥር 7 ነው ይላሉ። ይህንን ተከትሎ ዛሬ ...

Read More »

የተረጋጋ የትምህርት ፖሊሲ አለመኖር ወጣቱን ተስፋአልባ እንዲሆን አድርጎታል ተባለ፡፡

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጅማ ዩኒቨርስቲ ሰሞኑ በተደረገ አውደጥናት ላይ ፣ በየዓመቱ በየጊዜው የሚቀያየረው የትምህርት ፖሊሲ  ርእይ ያለው ወጣት እንዳይፈጠር ማድረጉ ተገልጿል ፡፡ ሀገሪቱ  ወጥ የሆነ የትምህርት ፖሊሲ ይዛ ባለመማራቷ ችግሩ መፈጠሩንም ምሁራን ተናግረዋል። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ማምጣት የቻሉ ብዙ ተማሪዎች በምደባ  ከፍላጐታቸው የራቀ ትምህርት እንዲያጠኑ በመደረጉ በአመት ከ12 ሺ በላይ ...

Read More »

ከሰሞኑ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የታሰረ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ተፈረደበት

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም በተጠራ ሰልፍ ላይ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል  ስድስትወርእንደተፈረደበት ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ጋዜጣው እንደሚለው ግንቦት 3/2007 ዓ.ምቄራየመጀመሪያ ፍርድቤት የቀረበው አቶ ስንታየሁ ፖሊስ በሰልፉ ወቅት ድንጋይ ወርወሯል በሚል በቀረበበትክስ  የስድስት ወር እስር ተፈርዶበታል፡፡ አቶስንታየሁመቃወሚያና የክስ ማቅለያ እንዲያቀርብ ተጠይቆ ‹‹የከሰሰኝኢህአዴግነው፡፡እየመሰከሩብኝያሉትምኢህአዴጎችናቸው፡፡የወሰነብኝምኢህአዴግነው፡፡በመሆኑምፍትህአገኛለሁብዬመቃወሚያምማቅለያምአላቀርብም›› ...

Read More »