የውጭ ሀገር ምንዛሪ ይዛችሁ ተንቀሳቅሳችኋል የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጎችና ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 1/2009)የውጭ ሀገር ምንዛሪ ይዛችሁ ተንቀሳቅሳችኋል የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጎችና ኢትዮጵያውያን በሳምንቱ መጨረሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የታሰሩት ግለሰቦች በአለም አቀፍና አህጉራዊ ተቋማት ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል። የውጭ ሀገር ምንዛሪ ይዛችሁ በሚል በተለይ በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ተነጣጥሯል በተባለው በዚህ የእስራት ዘመቻ በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የውጭ ዜጎችና ቤተሰቦቻቸው ጭምር ሰለባ መሆናቸው ...

Read More »

በአንድ ወጣት ልጆቻቸው የተደፈሩባቸው ወላጆች ፍትህ ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 28/2009) በአንድ ወጣት ልጆቻቸው የተደፈሩባቸው ወላጆች ፍትህ ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ። በአዲስ አበባ ጉለሌ አባዲና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ6 እስከ 8 አመት የሚሆናቸውን ዘጠኝ ህጻናት ወንዶችን የደፈረው ወጣት በእስር ላይ ቢሆንም እስካሁን ግን ፍትህ እንዳላገኙ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። የተደፈሩት ህጻናት ለከፍተኛ የጤናና የስነልቦና ችግር ተዳርገዋል። ሽንትና አይነምድራቸውን መቆጣጠር አልቻሉም።ወላጆቻቸው እንደሚሉት ህጻናቱን የደፈረው ወጣት ወላጅ አባት እያስፈራሯቸው ነው። በልጆቻቸው ላይ ከደረሰው ...

Read More »

በባህርዳር ከ50 በላይ ወጣቶች የተጨፈጨፉበትን ቀን ለማሰብ ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 28/2009) በአንድ ቀን ብቻ በህወሃት አጋዚያን ከ50 በላይ ወጣቶች የተጨፈጨፉበትን ቀን በሀዘን ለማስታወስ በባህር ዳር ነሐሴ 1/2009 ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ። የወጣቶቹን 1ኛ አመት ጅምላ ግድያ በሀዘን ለማስታወስ ከቤት ያለመውጣት አድማውን ለሰኞ የጠራው የባህርዳር ወጣቶች አስተባባሪ ኮሚቴ በሚል በህቡእ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው። በሕወሃት አጋዝያን ጭካኔ ኮብል በተባለ አካባቢ በአንድ ስፍራና ሰአት የተረፈረፉትን ወጣቶች ለማስታወስ የጎንደር ከተማ ህዝብም ከቤት ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዛሬ ተነሳ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 28/2009)ከመስከረም 28/2009 ጀምሮ ላለፉት 10 ወራት ተግባራዊ ሆኖ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዛሬ መነሳቱ ተገለጸ። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም በየክልሉ ሙሉ ስልጣን ተሰጥቶት የተሰማራው ኮማንድ ፖስት ስራውን እንደሚቀጥል በፓርላማው ይፋ ሆኗል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነሳ ተብሎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስራውን የጀመረው ኮማንድ ፖስት አለመፍረሱ አነጋጋሪ ሆኗል። ይህም መንግስት ከኢንቨስትመንትና ከቱሪዝም ጋር በተያያዘ የገጠመውን ቀውስ ለመሻገር ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ...

Read More »

የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዳይሬክተር ታሰሩ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 28/2009) የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዳይሬክተር ታሰሩ። የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ሁለቱ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ነው። ፓርላማው ዛሬ አርብ ሐምሌ 28/2009 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አለማየሁ ጉጆ ከፓርላማ ሲወጡ ወዲያው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። የመንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ...

Read More »

አቶ አዲሱ ለገሰ በባህርዳር ከሚገኘው ፓፒረስ ሆቴል የ75 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 27/2009)የቀድሞው የብአዴን ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ በባህርዳር ከሚገኘው ፓፒረስ ሆቴል የ75 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው የአካባቢው የደህንነት ሃላፊ ሆነው የቆዩት አቶ አያሌው መንገሻ ይፋ አደረጉ። አቶ አዲሱ ለገሰ በይፋ የፓፒረስ ሆቴል ባለቤት በመሆን ከሚታወቁትና አሁን በሕይወት ከሌሉት አቶ ጠብቀው ባሌ ጋር የንግድ ግንኙነት የጀመሩት የሽግግር መንግስቱ ጊዜ የባህርዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ምርቶችን እንዲያከፋፍሉ ያለጨረታ በመስጠት ...

Read More »

የመብራትና ውሃ እጥረት በመላ ሃገሪቱ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 27/2009) የመብራትና ውሃ እጥረት በመላ ሃገሪቱ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑን ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ። በመዲናይቱ አዲስ አበባ የኤሌክትሪክና የውሃ እጥረት እየተባባሰ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ንጽህና የጎደለው ውሃ ከመጠቀም ባለፈ ዝናብ እየጠበቁ ውሃ ማጠራቀምና ለእለታዊ ፍጆታ ማዋል እየተለመደ መጥቷል። በአማራ ክልልም የውሃና የኤሌክትሪክ እጥረቱ በህዝቡ ላይ የፈጠረው አደጋ እየከፋ መምጣቱ ተገልጿል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክፍልም በተለያዩ አካባቢዎች መብራትና ...

Read More »

በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተጣለው የቀን ገቢ ግብር እየተከፈለ እንዳልሆነ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 27/2009) የግብር መክፈያው የጊዜ ገደብ ሐምሌ 30 እየተቃረበ ቢመጣም በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች የንግዱ ማህበረሰብ የተጣለበትን የቀን ገቢ ግብር እየከፈለ እንዳልሆነ የደረሰን መረጃ አመለከተ። በአብዛኛው የአማራ ክልል ከተሞች ነጋዴው ግብር እንደማይከፍል በማስታወቁ የመንግስት ሃላፊዎች ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ እንደተጋቡ ተገልጿል። በሸዋ ሮቢት ለ4ኛ ቀን አድማው በቀጠለበት በዛሬው እለት ተሳትፈዋል የተባሉ የንግድ ቤቶች በመታሸግ ላይ ናቸው። በደብረታቦር ቤት ለቤት ቅስቀሳ በማድረግ ...

Read More »

አንድ የመከላከያ ባልደረባ የሆኑ ጄኔራል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 27/2009)አንድ የመከላከያ ባልደረባ የሆኑ ጄኔራል በሌብነት ወይንም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ይፋ ሆነ። ፓርላማው ለነገ የጠራው አስቸኳይ ስብሰባም ለምን እንደተጠራ ሳይነገር የሰአታት ጊዜ ቀርቶታል። የገዢው ፓርቲና የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ፓርላማው የተጠራው አዳዲስ ሚኒስትሮችን ለመሾም ጭምር እንደሆነ ገልጸዋል። የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ ሐሙስ 27/2009 ፍርድ ቤት የቀረቡት ብርጋዴር ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ የተባሉ የመከላከያ ...

Read More »

ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የተባበሩት መንግስታት የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ተደረጉ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 27/2009) በኢትዮጵያ ከሴቶች ወሊድ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ አገልግሎት የሰጡት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የተባበሩት መንግስታት የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ተደረጉ። ሽልማቱ የተሰጠው የተባበሩት መንግስታትን እሴቶች በበጎ ላስተዋወቁ አውስትራላውያን እውቅና በሚሰጠው ተቋም አማካኝነት ነው። ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የሕይወት ዘመናቸውን በኢትዮጵያ ለፌስቱላ የተጋለጡ 50ሺ ሴቶችን በመታደግ አገልግሎት የሰጡ አውስትራሊያዊ ሀኪም ናቸው ዶክተር ሐምሊን እድሜ ልካቸውን ከባለቤታቸው ጋር በመሆን በፌስቱላ የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያንን በመርዳት ...

Read More »