ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ነገ ስልጣናቸውን ሊለቁ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011)የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በነገው ዕለት በይፋ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ተገለጸ። ላለፉት አምስት አመታት በስልጣን ላይ የቆዩትንና የስልጣን ዘመናቸው ሊጠናቀቅ አንድ አመት ሲቀረው ስልጣን የሚለቁትን ዶክተር ሙላቱ ተሾመን የሚተካ ፕሬዝዳንት በነገው እለት እንደሚሰየምም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል። ከመስከረም 27/2006 ጀምሮ ላለፉት 5 አመታት በፕሬዝዳንትነት የቆዩትን ዶክተር ሙላቱ ተሾመን የሚተካው ማን እንደሆነ በይፋ ባይታወቅም፣አንዳንድ ምንጮች የብአዴኑ ዶክተር ...

Read More »

ከኦብነግ ጋር ስለ ህዝበ ውሳኔ የተነሳ ነገር የለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011)ከኦብነግ ጋር በተደረገው ስምምነት ስለመገንጠልም ሆነ ህዝበ ውሳኔ የተነሳ ነገር የለም ተባለ። የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ከድር የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ባለፈው ቅዳሜ በአስመራ የተደረሰውን ስምምነት አስመልክቶ ‘’በሶማሌ ክልል ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ ከመንግስት ጋር ተስማምተናል’’ ማለቱን በሬ ወለደ ተረር ተረት ነው ሲሉ አጣጥለውታል። ኦብነግ የሶማሌ ክልል ህዝብ እስከመገንጠል ድረስ ውሳኔ እንዲሰጥ ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ ደርሼ ...

Read More »

የአማራ ክልል ላወጣው መግለጫ ይቅርታ ይጠይቅ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011) የትግራይ ክልላዊ መንግስት በራያ ጉዳይ የአማራ ክልል ላወጣው መግለጫ የትግራይን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ  አሳሰበ። ትላንት ማምሻውን የወጣው የትግራይ ክልል መግለጫ የአማራ ክልል መንግስት የራያ ጉዳይ በሃይል መፍታት አይቻልም በሚል ላወጣው መግለጫ ምላሽ እንደሆነም ተመልክቷል። በአማራ ክልል መንግስት በኩል የወጣው መግለጫ መሰረታዊ የሆነ ሕገ መንግስታዊ ጥሰት ያለበትና በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ለዘመናት የኖረውን አብሮነት የሚጎዳ አደገኛ አካሄድ መሆኑን ...

Read More »

በራያ ቆቦና ዋጃ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011) በራያ ቆቦና ዋጃ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተሰማ። ህዝቡ መንገድ በመዝጋት የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ መግታቱን የደረሰን ዜና ያመለክታል። በራያ አላማጣ አፈናውና አፈሳው ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ መሆኑንም ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጸዋል። ባለፉት አራት ቀናት ከአላማጣ፣ ከዋጃ ከጡሙጋና ከቆቦ ራያ የታፈሱ ወጣቶች ወደየት እንደተወሰዱ እንደማያውቁ ቤተሰብ በስጋት በመግለጽ ላይ ነው። ከአላማጣ ከ10 በላይ የሀገር ሽማግሌዎችና የከተማዋ ታዋቂ ግለሰቦችም መታሰራቸው ታውቋል። በአዲስ አበባ ለዛሬ ...

Read More »

የትግራይ ክልል የአማራ ክልል ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳሰበ

የትግራይ ክልል የአማራ ክልል ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳሰበ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ/ም ) የትግራይ ክልል መንግስት፣ የአማራ ክልል መንግስት ጥቅምት 13 ቀን 2011 ዓም በወልቃይትና በራያ የማንነት ጥያቄዎች ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ የሚቃወም መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ በመግለጫውም “የትግራይ ክልል ከመግለጫው በተቃራኒ የሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ተወላጆች ሕገ መንግስታዊ መብታቸውና ነፃነታቸው ተከብሮ በሰላምና በክብር የሚኖሩባት ክልል ሆና እያለች ዜጎች በማንነታቸው ...

Read More »

የኦጋዴ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር የሶማሌ ክልል ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መስማማቱን ሲገልጽ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣን በድርድሩ ስለ ሕዝበ ውሳኔ የተነሳ ነገር የለም በማለት የኦብነግን መግለጫ ውድቅ አደረጉ።

የኦጋዴ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር የሶማሌ ክልል ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መስማማቱን ሲገልጽ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣን በድርድሩ ስለ ሕዝበ ውሳኔ የተነሳ ነገር የለም በማለት የኦብነግን መግለጫ ውድቅ አደረጉ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ/ም ) ኦብነግ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ በሰላማዊ መንገድ እንዲታገል በኢትዮጵያ መንግስትና በግንባሩ መካከል በአስመራ ሲደረግ የነበረው ድርድር በስምምነት መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ...

Read More »

የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 13/2011) የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ። https://www.ethiopiatrustfund.org/ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በይፋ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ በፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም የሚመራ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት አማካሪ ቦርድ መሰየሙም ይታወሳል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት የሚኖሩ ችግረኛ ዜጎችን ለመደገፍ በቀን አንድ ዶላር እንዲያዋጡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተቋቋመው አማካሪ ቦርድ ትላንት በይፋ መርሃ ግብሩ መጀመሩን አስታውቋል። በዚህም ...

Read More »

በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ቀጥሏል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 13/2011) በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት መቀጠሉ ተገለጸ። ተጨማሪ ተፈናቃዮች መመዝገባቸውን የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳደር አስታውቋል። በሁለቱ ክልሎች ውስጥ የሚኖረውን ህዝብ በአሉባልታ በመንዳት ለግጭት የሚዳርጉ ሃይሎች መኖራቸውን የምዕራብ ወለጋ ዞን ጸጥታና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዋጋሪ ቀጄላ ለመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ግጭቱ ከተጠበቀው በላይ እየሰፋ መጥቷል። ተፈናቃዮቹን ለመመለስ የተደረገው ስምምነት ተግባራዊ ባለመሆኑ ችግሩ እየከፋ ...

Read More »

የአማራ ክልል መንግስት የራያንና ወልቃይት ጥያቄዎችን በሃይል ለመፍታት የሚደረገው ሙከራ መፍትሄ አያመጣም አለ

የአማራ ክልል መንግስት የራያንና ወልቃይት ጥያቄዎችን በሃይል ለመፍታት የሚደረገው ሙከራ መፍትሄ አያመጣም አለ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 13 ቀን 2011 ዓ/ም ) ክልሉ ጥቅምት 13 ቀን 2011 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ “የአማራ ብሔራዊ ክልል ከትግራይ ብሔራዊ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የወልቃይትና ራያ አላማጣ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች የሰላም መታወክ” እየገጠመው መሆኑን ጠቅሷል። በወልቃይት አካባቢ በማንነታችን ብቻ ጥቃት ደረሰብን ያሉ የወልቃይት አማራዎች ተፈናቅለው በጐንደር ...

Read More »

ታዋቂው የማሲንቆ ተጫዋች ለገሠ አብዲ የቀብር ስነስርአት ተፈፀመ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011)በኦሮምኛ ሙዚቃ ታዋቂው የማሲንቆ ተጫዋች ለገሠ አብዲ  የቀብር ስነስርአት ዛሬ ተፈፀመ። የአርቲስቱ የቀብር ስነስርአት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሲፈጸም ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና አድናቂዎቻቸው ተገኝተዋል። አንጋፋው የኦሮምኛ ማሲንቆ ተጫዋች ለገሠ አብዲ በ1927 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ሰላሌ ያያ ቃጫማ በተባለ ስፍራ ነው የተወለዱት። በኦሮምኛ የሙዚቃ አድማጮች የማሲንቆው ንጉስ ተብለው የሚጠሩት ለገሰ አብዲ በሀገር ፍቅር፥ በብሄራዊ ቴአትር፣ በአዲስ አበባ ከተማ ...

Read More »