የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እድገት ዜና ባዶ ፕሮፓጋንዳ ነው ሲሉ አጣጣሉት

ሰኔ ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ የተለያዩ ኢኮሚስቶችን በማናገር እንደዘገበው ኢትዮጵያ በማንፋክቸሪንግ ዘረፍ ከፍተኛ እድገት እንዳገኘች ተደርጎ የሚቀርበው ዘገባ ባዶ ፕሮፓጋንዳ ነው ብሎአል። ኢትዮጵያ እንኳንስ አፍሪካ ምሳሌ ልትሆን በማንፋክቸሪንግ ዘረፍ፣ ከአፍሪካ አገራት ያነሰ ስራ መስራቱዋን ጋዜጣው ዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግስት የተሳካላት ነገር ቢኖር፣ አገሪቱ በኢንዱስትሪው ዘርፍ እያደገች ነው የሚለውን ፕሮፓጋንዳ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማድረግ ...

Read More »

በሽብርተኝነት ሥም ተከሰው በእስር ሲሰቃዩ ከነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መካከል ስድስቱ ነጻ ተባሉ

ሰኔ ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ ተይዘው የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ለዓመታት በእስር ቤት ሲሰቃዩ የነበሩት ስድስት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ከቀረበባቸው ክስ ነጻ ተብለው ተለቀዋል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰኔ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን፣ 4ኛ ተከሳሽ አቶ አወቀ ሞኙ ሆዴ፣ 8ኛ ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ 10ኛ ...

Read More »

በአፋር ክልል ከአርታሌ የሚወጣው የጨው ክምችት “የመቀሌ ጨው” እየተባለ ለገበያ መቅረቡ በአፋር አክቲቪስቶች ዘንድ ቁጣ ቀሰቀሰ

ሰኔ ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሰባ አቶ ገአስ አህመድና አክቲቪስት አካድር ኢብራሂም በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት በአርታሌ፣ በዳሎል እና በሌሎች ከፍተኛ የጨው ክምችት የሚገኙባቸው የአፋር ቦታዎች ቀደም ካሉት ዓመታት ጀምሮ በጨው ማምረት ኢንቨስትመንት የተሰማሩት በሙሉ የህወኃት ደጋፊዎች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ባለሀብቶቹ ከአርታሌና አካባቢው በየዓመቱ በሚሊዮን ኩንታል የሚገመት ጨው በማውጣትና ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተከሰተው የሰብል ተምች በአሳሳቢ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተከሰተው የሰብል ተምች በአሳሳቢ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ። የሰብል ተምቹ እስካሁን ባለው ሁኔታ በደቡብ ክልል ያሉትን ሁሉንም ዞኖች ያጠቃ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በኦሮሚያ ደግሞ ሰባት የሚሆኑ ዞኖች እየተስፋፋ ባለው የሰብል ተምች መጎዳታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል።  ተምቹ የምስራቅና የምዕራብ አማራ ክልል አካባቢዎችን እንዲሁም በጋምቤላ እኛ ቤኒሻንጉል ጉምዝም ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። የኢትዮጵያ ...

Read More »

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዋሽንግተን ዲሲ ተቃውሞ ገጠማቸው

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2009) በቅርቡ ለአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት የተመረጡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዋሽንግተን ዲሲ ተቃውሞ ገጠማቸው። በዩ ኤስ አሜሪካ ርዕሰ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ አለም ባንክ ጽ/ቤት ደጃፍ ተቃውሞ የቀረበባቸው የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  አባልና የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የተቃውሞ ድምፅ እየተከተላቸው አካባቢውን ሲለቁ ታይተዋል።   ለአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት በዕጩነት መወዳደራቸውን በመቃወም የተጀመረው ...

Read More »

በየመን የኮሌራ በሽታ እየተስፋፋ ነው

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2009) በጦርነት በምትታመሰው የመን የኮሌራ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ። በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ 940 ሰዎች በላይ በበሽታው መሞታቸው የታወቀ ሲሆን በሚቀጥሉት ጥቂት ወራትም ከ300 ሺ በላይ ሰዎች በላይ ሊያዙ እንደሚችሉ ተገልጿል። በተበከለ ውሃና ምግብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ የሚገኘው የኮሌራ በሽታ፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት የስርጭት ሂደቱ ከሶስት እጥፍ በላይ በማደግ 5,400 አዳዲስ የበሽታው ተጠቂዎች ...

Read More »

የከባቢ አየር ሙቀት መጨመር በኢትዮጵያ የወባ በሽታ እንዲስፋፋ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የከባቢ አየር ጸባይ ሙቀት መጨመር ለወባ በሽታ መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረገ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ። በዝቅተኛና ሞቃታማ ቦታዎች ይራቡ የነበሩ የወባ በሽታ አስተላላፊ ትንኞች በሙቀቱ ምክንያት ህዝብ በብዛት ወደሚኖርባቸው ቀዝቃዛና ደጋማ የነበሩ ቦታዎች በመዛመት ላይ መሆናቸውን ጥናቱ አመልክቷል።  በሜይን ዩኒቨርስቲና በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ አለም አቀፍ የአየርጸባይና የማህበረሰብ ጥናት ኢንስቲቲዩት  ትብብር የተደረገው ይኸው ጥናት እንዳመለከተው አብዛኛው ...

Read More »

አኤሳዋን  የስፖርት ማህበር የ2017 ፕሮግራሞቹን ለመሰረዝ ተገደደ

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2009) በሰሜን አሜሪካ “የሃገር ውስጥ ገቢ ህግ” መሰረት ትርፋማ ባልሆነ እና ከታክስ ነጻ በሆነ መልኩ ከ2011 ጀምሮ የተቋቋመው “አኤሳዋን” የስፖርት ማህበር የ2017 ፕሮግራሙን ለመሰረዝ መገደዱን የቀድሞ የስፖርት ማህበሩ አመራሮች ለኢሳት ገለጹ። እነዚሁ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቀድሞ የስፖርት ማህበሩ አመራሮች “አኤሳዋን” ላለፉት አምስት አመታት ያካሄደው ፕሮግራም በዝግጅቶች እጥረት ድርቅ በመመታቱና ታዋቂ ድምጻውያን የኪነጥበብ ሙያተኞች በዝግጅቱ ላይ ለመሳተፍ ...

Read More »

በሊቢያ የታገቱ 260 ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን ሁኔታ እንዳሳሰበው አለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም ገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2009) በሊቢያ በህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎችና በወንጀለኛ ቡድኖች ተይዘው የሚገኙ ወደ 260 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን ስደተኞች ሁኔታ እጅግ እንዳሳሰበው አለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) አስታወቀ። በእነዚህ ቡድኖች ተይዘው የሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውን ስደተኞች መካከል ብዛት ያላቸው ህጻናት እንደሚገኙበት ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።   ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን እየተሰራጨ የሚኘውን ቪዲዮ ዋቢ በማድረግ ስጋቱን የገለጸው የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ...

Read More »

በለንደን ግሪንፊልድ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ 5 ኢትዮጵያውያን ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2009) በእንግሊዝ ለንደን ግሪንፊልድ ህንጻ ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ኢትዮጵያውያን ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነገረ።  በ28ኛው ፎቅ ላይ የነበሩት አባት፣ እናትና 3 ልጆቻቸው በቃጠሎው ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተፈርቷል። ልጆቹ የ5፣ የ12 እና የ14 አመት ዕድሜ ያላቸው መሆናቸው ታውቋል። በለንደኑ ቃጠሎ እስካሁን የ17ቱ ሰዎች ሞት ሲረጋገጥ 18ቱ ደግሞ በሞትና በህይወት መካከል ክፉኛ ቆስለው እንደሚገኙ ተነግሯል። ...

Read More »