በጋይንት የአርበኛ ግንቦት ሰባት ታጋዮች በብዓዴን ጽ/ቤት ላይ ጥቃት ሰነዘሩ

ኢሳት (መጋቢት 14 ፥ 2009) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በጋይንት ከተማ የአርበኛ ግንቦት ሰባት ታጋዮች በብዓዴን ጽ/ቤት ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተሰማ። በከተማዋ የአስተዳደር እና ጸጥታ መረጃ ሃላፊ መኖሪያ ቤት የቦንብ ጥቃት ተፈጽሞበታል። በወገራ ወረዳ እና ሌሎች አካባቢዎች በተሰነዘረው ጥቃት ደግሞ የህወሃት/ኢህአዴግ  ወታደሮች ተገድለዋል። ጥቃቱ የተሰነዘረው በመከላከያና በጸረ-ሽምቅ ሚሊሺያዎችና መደበኛ የፖሊስ አባላት ላይ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ...

Read More »

የድርቅ አደጋ ተባብሶ ሊቀጥል እንደሚችል ተመድ አስታወቀ

ኢሳት (መጋቢት 14 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ዳግም ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ከተያዘው ወር ጀምሮ እስከ መስከረም ወር ድረስ እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። የድርቁ አደጋ በተለይ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል በሚገኙት የዋርዴር እና የኮራህ ዞኖች የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ የምግብ እጥረቱ ወደ ረሃብ ደረጃ ለመሸጋጋር አንድ ደረጃ ብቻ እንደቀረው ድርጅቱ ይፋ አድጓል። ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ መገኘት ያለበት ድጋፍ በወቅቱ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ለኢሳት በላከው መረጃ መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓም የግንባሩ ታጋዮች ወደ ጋይንት ከተማ በመግባት ከምሽቱ 2 ሰአት ተኩል ላይ በብአዴን ጽ/ቤት እና ሹመት በተባለው አስተዳደር እና ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ ቦንብ በመወርወር ጉዳት ማድረሳቸውንና ማሽቱም በተኩስ ሲናወጥ ማደሩን ገልጿል። ሹመት የተባለው የደህንነት አባል ከዚህ በፊት በተደረገው ህዝባዊ አመጽ ...

Read More »

በሃረር በከፍተኛ የውሃ ችግር ተከስቷል። ከ1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ያላነሰ ገንዘብ የወጣባቸው ፕሮጀክቶች ተቋርጠዋል።

መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ የ747 ሚሊዮን 175 ሺ ብር ብድር የተሰራው የሃሳሊሶ የውሃ ፐሮጀክት ለ30 አመታት ለ350 ሺ ህዝብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንደሚያቀርብ፣ በ2004 ዓም ሲመረቅ የመንግስት ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፣ ፕሮጀክቱ ውሃው ሸሽቷል በሚል ምክንያት ተመርቆ 2 አመታት እንኳ በአግባቡ ሳያገለግል የተዘጋ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት ሃረር በከፍተኛ ...

Read More »

በባህርዳር በሚካሄድ የቤት ማፍረስ ዘመቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጠለያ አልባ ሆኑ

መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ያለምንም ተለዋጭ ቤትና ቦታ ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉት፣ በቀበሌ 14 አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ትናንት ባሉዋን ሲደበድቡባት ጩኸት ያሰማች ነፍሰጡር ሴት ፣ በፖሊሶች በደረሰባት ድብደባ ከፉኛ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች። አንድ ህጻንም በነበረው ግርግር ተረጋግጣ ህይወታ ማለፉ ታውቋል። አብዛኞቹ ወጣቶች ጫካ በመግባት ከድብደባ አምልጠዋል። ሁኔታው አስከፊ መሆኑን የሚናገሩት ...

Read More »

የገጠሩ ህዝብ የኢህአዴግን ጥሪ መቀበል አቁሟል ሲሉ የወረዳ አመራሮች ተናገሩ

መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በከተማው ህዝብ ሳይሆን በአርሶ አደሩ ድጋፍ እንደሚተማመን በተደጋጋሚ ይገ ልጸል። ምንም እንኳ አሁንም ከ6 ሚሊዮን ያላነሰ አርሶአደር በረሃብ መጠቃቱ እንዲሁም ከ7 ሚሊዮን ያላነሰ አርሶአደር በምግብ ለስራ መርሃ ግብር ታቅፎ በውጭ እርዳታ እየኖረ ቢሆንም፣ ኢህአዴግ የግብርና ምርቱ በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ይናገራል። አርሶአደሩም መሰረታዊ የሚባሉት የምግብ፣ የጤና፣ የትምህርት ፍላጎቱ እየተሟሉለት መሆኑን ግንባሩ ...

Read More »

ህዝብ ባደረሰው ጫና _የወረዳ 10 አስተዳደር ያወጣውን ማስታወቂያ ካደ

መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 10 ከቤት መፈናቀል ጋር በተያያዘ ወረዳው ያወጣውን ማስታወቂያ ለመገንጠልና በዱሪዬዎች የተለጠፈ ነው በሚል ሰበብ በመካድ ለማስተባበል መሞከሩን ነዋሪዎች ተናገሩ። በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች እስከ ግንቦት 30 ቀን 2009 ዓም ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ በስብሰባ ላይ የተነገራቸው መሆኑን ኢሳት ዘግቦ የነበረ ሲሆን፣ መጋቢት12 ደግሞ “መንግስት መሬቱን ለቻይናና ቱርክ ባለሃብቶች ማስረከብ ስላለበት ...

Read More »

በአሜሪካ በተዘጋጀ የአፍሪካ የንግድ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተጋበዙ አፍሪካውያን የመግቢያ ቪዛ ተከለከሉ

መጋቢት 13: 2009) ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት በአሜሪካ በተዘጋጀ የአፍሪካ የንግድ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተጋበዙ እንግዶች የአሜሪካ የመግቢያ ቪዛ መከልከላቸውን የጉባዔው አዘጋጆች አስታወቁ። በካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኘ የደቡብ ካለፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የተዘጋጀው የንግድ ጉባዔ በአፍሪካ ጉዳይ ላይ ለመምከር ቢዘጋጅም አንድም የአፍሪካ ተወካይ በቪዛ ችግር ሊገኝ አለመቻሉን ዘጋርዲያን ጋዜጣ አዘጋጆቹን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ለሶስት ቀናት የተዘጋጀው የንግድ ጉባዔ የአፍሪካና የአሜሪካንን የቢዝነስ ትስስር ...

Read More »

በአዲስ አበባ የውሃ እጥረት ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ

መጋቢት 13: 2009) በአዲስ አባባ በርካታ አካባቢዎች የውሃ እጥረት ችግር ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች አስታወቁ። የከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለከተማዋ የውሃ አቅርቦት የሚያገለግሉ ጉድጓዶች በመድረቃቸው ምክንያት የውሃ እጥረቱ መከሰቱን በቅርቡ መግለፁ ይታወሳል። ባለስልጣኑ የውሃ እጥረቱ ጊዜያዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ተደርጓል ሲል ከቀናት በፊት መግለጫን ቢሰጥም ነዋሪዎችና የተቋማት ባለቤቶች ችግሩ ዕልባት አለማግኘቱን ይገልጻሉ። ለአመታት የቆየው የመዲናይቱ የውሃ እንዲሁም የመብራት እጥረት በዕለት ከእለት ኑሯቸው ...

Read More »

በአዲስ አበባ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ

መጋቢት 13: 2009) በአዲስ አበባ ለሁለተኛ ሳምንት ጊዜ የቀጠለው የነዳጅ እጥረት በነዋሪዎች ላይ ማህበራዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጹ። በተለይ የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቅመው የተለያዩ ጉዳዮች የሚያከናውኑ ነዋሪዎች የነዳጅ እጥረቱ ለሁለተኛ ሳምንት በመቀጠሉ ምክንያት ለዘርፉ ብዙ ችግር መዳረጋቸውን አስታወቀዋል። በመዲናይቱ የሚገኙ የተሽከርካሪ ባለሃብቶች በበኩላቸው ነዳጅ ለማግኘት በነዳጅ ማደያ አካባቢዎች ለማደር መገደዳቸውን ጭምር ለመገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል። ለመንግስት ስራና ለግል ጉዳዩች ለመንቀሳቀስ የህዝብ ...

Read More »