በጣና ሃይቅ ዳርቻ በሚገኙ ከተሞች የመሬት ቅርምቱ ጨምሯል

ሰኔ ፲፪( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣቶች በተወለድንበት ምድር ነጻነት አጥተናል ይላሉ በጣና ሃይቅ ዳርቻ በሚገኙ በጎርጎራ ፣ቁንዝላና ባህርዳር ከተሞች ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደተናጉሩት “ የጣና ሃይቅ አካባቢ በልማት ስም ተሸንሽኖ በመሰጠቱና ለአመታት ያለምንም ስራ ታጥረው በመቀመጣቸው ህዝቡ እየተቸገረ ነው። በጎርጎራና ዙሪያዋ ለ23 ዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች አሉ። አርሶአደሮች የእርሻ መሬት አጥተው በችግር ላይ ናቸው። ...

Read More »

የኮልፌ ቀራኒዮ ነዋሪዎች ጥያቄያቸውን እንዳያቀርቡ ታገዱ

ሰኔ ፲፪( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በኮልፈ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ካራ ቆሬ/ ሬጲ አካባቢ ሰኔ 03 ቀን 2009 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ በከፍተኛ ቃጠሎ የጋየውን የሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ተከትሎ እሁድ ሰኔ 4/09 ከ 1200 በላይ ነዋሪዎችን የሚወክሉ 205 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ለ3 ሠዓታት ያክል ተሰብስበው ፋብሪካው በህብረተሰቡ ላይ ያደረሰውን ጉዳት በዝርዝር በመጻፍ ለመስተዳድር ባለስልጣናት ...

Read More »

በምስራቅ ኢትዮጵያ ጥንታዊ የንግድ ማዕከል ተገኘ

ሰኔ 9 ፥ 2009 በምስራቅ ኢትዮጵያ ሃርላ በሚባል አካባቢ በመሰማራት ቁፋሮ ሲያደርጉ የነበሩ የስነ ምድር ተመራማሪዎች ከክርስቶስ ልደት በፊት በ10ኛው ክፍለ ዘመን የንግድ ማዕከል የነበረ አንድ ከተማ ማግኘታቸውን ገለጹ። ከግብጽ፣ ከህንድና፣ ከቻይና ወደ ከተማው የገቡ  የተለያዩ ቁሳቁሶችም መገኘታቸው ተገልጿል። ከማዳጋስካር፣ ከማልዲቭስ እና ከየመን ጭምር የመጡ የተለያዩ ጌጣጌቶች በአካባቢው ተቀብረው መገኘታቸው ቢቢሲ በድረገጹ አስነብቧል።  ከዚህ በተጨማሪ የስነ-ምድር ተመራማሪዎች በ12ኛው ክ/ዘመን የተገነባ ...

Read More »

የሽብር ወንጀል ፈጽማችኋል በሚል በተከሰሱት ኢትዮጵያውያን ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈ

ሰኔ 9 ፥ 2009 የሽብር ወንጀል ፈጽማችኋል በሚል በተለያዩ የክስ መዝገቦች በወህኒ ቤት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ውስጥ በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ የጥፋተኘነት ውሳኔ ተሰጠ። ከ13ቱ ተከሳሾች 7ቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲተለለፍባቸው፣ 6ቱ በነጻ እንዲሰናበቱ ተወስኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታሰሩ ዳንዔል ሺበሺና ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እንዲከላከሉ ፍ/ቤት ወሰነ። ከግንቦት 7 ጋር በተየያዘ ክስ የተመሰረተባቸውና በአሸባሪነት ተወንጅለው ለአመታት ...

Read More »

የኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከመቼው በላይ ዝቅተኛ ነው ተባለ

ሰኔ 9 ፥ 2009 የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከመቼው ጊዜ እጅግ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። ዘርፉ እያበረከተ ያለው አስተዋጽዖም ባለፉት 40 በላይ አመታት እጅግ ዝቀተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል። ጋዜጣው የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ለአገሪቷ ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከሁሉም የአፍሪካ ሃገራት እጅግ ዝቅተኛ ውጤት ማስመዝገቡን የአለም ባንክን መረጃ ጠቅሶ ዘግቧል። በመሆኑም፣ መስኩ እኤአ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአማራ ባለሃብቶች ላይ በደል እየፈጸመ ነው ሲሉ የክልሉ ከፍተኛ ባለስጣናት ተናገሩ

ሰኔ ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በባህርዳር ከተማ የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከባለሃብቶች እና አበዳሪ አካላት ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኪሚሽነር አቶ መላኩ አለበል፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአማራ ባለሃብቶች ላይ በደል እየፈጸመው ነው ብለዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደረጃ ንግድ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋየ ጌታቸውም፣ በክልሉ ውስጥ ያሉ ባለሃብቶች ...

Read More »

የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እድገት ዜና ባዶ ፕሮፓጋንዳ ነው ሲሉ አጣጣሉት

ሰኔ ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ የተለያዩ ኢኮሚስቶችን በማናገር እንደዘገበው ኢትዮጵያ በማንፋክቸሪንግ ዘረፍ ከፍተኛ እድገት እንዳገኘች ተደርጎ የሚቀርበው ዘገባ ባዶ ፕሮፓጋንዳ ነው ብሎአል። ኢትዮጵያ እንኳንስ አፍሪካ ምሳሌ ልትሆን በማንፋክቸሪንግ ዘረፍ፣ ከአፍሪካ አገራት ያነሰ ስራ መስራቱዋን ጋዜጣው ዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግስት የተሳካላት ነገር ቢኖር፣ አገሪቱ በኢንዱስትሪው ዘርፍ እያደገች ነው የሚለውን ፕሮፓጋንዳ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማድረግ ...

Read More »

በሽብርተኝነት ሥም ተከሰው በእስር ሲሰቃዩ ከነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መካከል ስድስቱ ነጻ ተባሉ

ሰኔ ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ ተይዘው የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ለዓመታት በእስር ቤት ሲሰቃዩ የነበሩት ስድስት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ከቀረበባቸው ክስ ነጻ ተብለው ተለቀዋል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰኔ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን፣ 4ኛ ተከሳሽ አቶ አወቀ ሞኙ ሆዴ፣ 8ኛ ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ 10ኛ ...

Read More »

በአፋር ክልል ከአርታሌ የሚወጣው የጨው ክምችት “የመቀሌ ጨው” እየተባለ ለገበያ መቅረቡ በአፋር አክቲቪስቶች ዘንድ ቁጣ ቀሰቀሰ

ሰኔ ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሰባ አቶ ገአስ አህመድና አክቲቪስት አካድር ኢብራሂም በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት በአርታሌ፣ በዳሎል እና በሌሎች ከፍተኛ የጨው ክምችት የሚገኙባቸው የአፋር ቦታዎች ቀደም ካሉት ዓመታት ጀምሮ በጨው ማምረት ኢንቨስትመንት የተሰማሩት በሙሉ የህወኃት ደጋፊዎች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ባለሀብቶቹ ከአርታሌና አካባቢው በየዓመቱ በሚሊዮን ኩንታል የሚገመት ጨው በማውጣትና ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተከሰተው የሰብል ተምች በአሳሳቢ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተከሰተው የሰብል ተምች በአሳሳቢ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ። የሰብል ተምቹ እስካሁን ባለው ሁኔታ በደቡብ ክልል ያሉትን ሁሉንም ዞኖች ያጠቃ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በኦሮሚያ ደግሞ ሰባት የሚሆኑ ዞኖች እየተስፋፋ ባለው የሰብል ተምች መጎዳታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል።  ተምቹ የምስራቅና የምዕራብ አማራ ክልል አካባቢዎችን እንዲሁም በጋምቤላ እኛ ቤኒሻንጉል ጉምዝም ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። የኢትዮጵያ ...

Read More »