የሰራዊቱ አባላት ከትግራይ እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉ ተገቢ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 01/2011) የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎችና የሰራዊቱ አባላት ከትግራይ እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉ ተገቢ አይደለም ሲሉ ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ገለጹ። በማንኛውም መልኩ ግጭትና ጦርነት የሚቀሰቅስን ተግባር አንቀበልም ያሉት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የህዝቡን ስጋት ብንረዳም የጦር መሳሪያዎቹ የፌደራሉ መንግስት ንብረት በመሆናቸው የመሳሪያውንና የሰራዊቱን ስምሪት የምንወስነው እኛ ሳንሆን የፌደራሉ መንግስት ነው ብለዋል። በትግራይ ህዝብ ሽፋን አድርገው ትርምስ ለመፍጠር የሚሞክሩ ወገኖች መኖራቸውን ገልጸዋል። ...

Read More »

በምዕራብ ኢትዮጵያ ግለሰቦችና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 1/2011) የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በምዕራብ ኢትዮጵያ ሕግና ስርአትን ለማስከበር በጀመረው ርምጃ 171 ግለሰቦች እንዲሁም የጦር መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ትጥቅ የማስፈታቱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ በምዕራብ ኢትዮጵያ ጦርነት ተከፍቶብኛል፣ሶስተኛ ወገን ባለበት እንደራደር በማለት መግለጫ ማውጣቱም አይዘነጋም። የሃገር መከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ...

Read More »

በምዕራብ ጎንደር ዞን 8 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 1/2011) በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በኮኪትና ገንዳ ውሃ ከተሞች በመከላከያ ሰራዊት በተወሰደ ርምጃ 8 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ትላንት ገንዳውሃና ኮኪት በተባሉ አካባቢዎች ለተቃውሞ በወጡ ነዋሪዎችና በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል በተፈጠረ ግጭት ስምንት ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። የሱር ኮንስትራክሽን ተሽከርካሪዎች አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በነዋሪው ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ነው ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ግጭቱ የተፈጠረው። ህዝቡ መከላከያ ሰራዊቱ ከአካባቢው እንዲለቅ ጠይቋል። የትግራይ ...

Read More »

በጋቦን የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2011)በማዕከላዊ አፍሪካ ክፍል በምትገኘው ጋቦን የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ያደረጉት ሁለት ወታደሮች ሲገደሉ 3ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘገበ። ከግልበጣው ሙከራ ጀርባ አሉ ተብለው በተጠረጠሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና የሲቪል ድርጅት ሃላፊዎች ላይ ምርመራ እንደሚካሄድም የጋቦን መንግስት አስታውቋል። እሁድ ሌሊት 10 ሰዓት ተኩል ላይ የሃገሪቱን የሬዲዮና የቴሌቭዥን ጣቢያዎች በመቆጣጠር ለግማሽ ክፍለ ዘመን የዘለቀው የቦንጎ ቤተሰብ አገዛዝ ማብቃቱን የገለጹት ...

Read More »

በመከላከያ ሰራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት ሊቋቋም ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2011) በኢትዮጵያ በአንዳንድ የሃገሪቱ ክልሎች ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት በመከላከያ ሰራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት በመቋቋም ላይ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሯ ገለጹ። የሃገር መከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ለፓርላማው ዛሬ እንደገለጹት በክልሎች ጥያቄ ጸጥታ ወደ ደፈረሰባቸው አካባቢዎች የገባው የመከላከያ ሰራዊት የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ባለፉት 6 ወራት ከ7ሺህ በላይ የሰራዊት አባላት መሰናበታቸውንም ገልጸዋል። ቦታዎቹ ወይንም ክልሎቹ የትኞቹ እንደሆኑ ...

Read More »

ኦነግ በምዕራብ ኦሮሚያ ጦርነት ተከፈተብኝ አለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2011) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ በምዕራብ ኦሮሚያ ጦርነት እንደተከፈተበት ገለጸ። ሶስተኛ ወገን ባለበት ከመንግስት ጋር ለመደራደር ያለውንም ዝግጅት ገልጿል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ “ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጦርነቱ ቆሞ ስምምነታችን ሊታደስና ሊጠናከር ይገባል” በሚል ርዕስ ትላንት ታህሳስ 29/2011 ባወጣው መግለጫ ኢህአዴግ ከኦነግ ጋር የደረሱበትን ስምምነት በመጣስ በኦሮሚያ ክልል በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ ጦርነት እንደተከፈተበት ገልጿል። ኢህአዴግና በርሱ የሚመራው መንግስት ከጸረ-ዲሞክራሲ ...

Read More »

የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2011) የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ስራ አስፈጻሚ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ እየመከረ መሆኑ ተነገረ። የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው ስብሰባ በአማራ ክልል ባሉ ፖለቲካዊና የህዝብ ችግሮች ጉዳይ ላይ ይመክራል ተብሏል። በአጠቃላይ  በሃገራዊ ጉዳዮች ላይም እንደሚነጋገር ተገልጿል። ህወሃት በቅርቡ ባካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የሃገሪቱ ጸጥታና ደህንነት እንዳሰባሰበውና ኢህአዴግ አስቸኳይ የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ እንዲጠራ እንደሚፈልግም አስታውቋል። የአዴፓ ስራ ...

Read More »

የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ ተገታ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2011)የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ በድጋሚ መገታቱ ተሰማ። የሽሬ ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች እንዳያልፉ ማገታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በመንግስት ውሳኔ ሰራዊቱ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ትዕዛዝ ቢሰጠውም ህዝብ መንገድ በመዝጋት የሰራዊቱን ግስጋሴ ማስቆሙ ታውቋል። በርካታ የመከላከያ ተሽከርካሪዎች በሽሬ ከተማ በሚገኝ ስታዲየም እንዲገባ መደረጉ ተገልጿል። የሽሬ ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ላይ ተቃውሞ በማሰማት የመከላከያ ተሽከርካሪዎችና መሳሪያዎችን እንደማይለቁ አስታውቀዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ እንቅስቃሴው ...

Read More »

ሳውዲ የሴቶችን መብት የሚጠብቁ ተጨማሪ ርምጃዎችን ተግባራዊ አደረገች

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 29/2011) የሳውዲአረቢያው አልጋወራሽ የሴቶችን መብት የሚጠብቁ ተጨማሪ ርምጃዎችን ተግባራዊ አደረጉ። የሳውዲ አረቢያ ሴቶች ጋብቻቸው መፍረሱን የሚያውቁበት ዕድልና መብት ተነፍገው ቢቆዩም ከትናንት ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው መመሪያ ወንዱ ጋብቻውን አልፈልግም ብሎ ፍቺ ሲጠይቅና ሲፈጸምለት ለባለቤትየው ትዳርሽ ፈርሷል የሚል የጽሁፍ መልዕክት እንዲደርሳት ተወስኖ ተግባራዊ ሆኗል። ቀደም ብሎ በነበረው አሰራር ሴቷ ትዳርዋ ይፍረስ አይፍረስ የምታውቅበት ሁኔታ አልነበረም። በሳውዲ አረቢያ ከትናንት ጀምሮ ማሻሻያ ...

Read More »

የአፋር ህዝብ ፓርቲ በሃገር ቤት በይፋ መንቀሳቀስ ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 29/2011)የአፋር ህዝብ ፓርቲ በአፋር ክልል በሁለት ከተሞች ጽሕፈት ቤት በመክፈት በሃገር ቤት በይፋ መንቀሳቀስ ጀመረ። የመጀመሪውያውንም ጉባዔ ማካሄዱን አስታወቋል። ፓርቲው ከምርጫ ቦርድ የመንቀሳቀሻ ፍቃድ እንደተሰጠውም ታውቋል። በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የፓርቲ እውቅና እስኪያገኝ በጊዜያዊነት በተሰጠው ፍቃድ በአፋር ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ተጨማሪ ጽሕፈት ቤቶችን ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል። ባለፈው ቅዳሜ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹ በተገኙበት የጽህፈት ቤት ምረቃት ያደረገው የአፋር ...

Read More »