ኢትዮጵያ የሰላምና የወዳጅነት እግር ኳስ ዋንጫ ላይ ልትሳተፍ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2011)ኢትዮጵያ በአስመራ በሚካሄደው የሰላምና የወዳጅነት እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ አስታወቀች፡፡ የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን አራት ሀገራት ይካፈሉበታል ተብሎ በሚጠበቀውና በአስመራ አስተናጋጅነት በሚካሄደው “የሠላም እና የወዳጅነት ዋንጫ” ላይ ይሳተፋል ተብሏል። በየካቲት ወር በአስመራ አስተናጋጅነት በሚካሄደውና በኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ወጣት ቡድኖች መካከል በሚደረገው ‘የሠላም እና ወዳጅነት ዋንጫ’ ላይ የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን እንደሚሳተፍ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል። የአራቱን ...

Read More »

በምዕራብ ጎንደር የተፈጸመው ግድያ ኃላፊነት የጎደለው ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/ 2011) በመከላከያ ሰራዊት አባላት በምዕራብ ጎንደር መተማ አካባቢ የተፈጸመው ግድያ ኃላፊነት የጎደለውና ትክክለኛ ያለመሆኑን የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ እንዳርጋቸው ገለጹ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስለጉዳዩ ትናንት በሰጡት መግለጫ  በደረሰው ጉዳት ኃላፊነት መውሰድ ያለበት አካል ኃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል ብለዋል። ይሕ በእንዲህ እንዳለም የአዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ትናንት ማጠናቀቁን ዘገባዎች አመልክተዋል። ...

Read More »

በጣና በለስ ከሦስት ሺህ በላይ ሰዎች ለከፋ ረሀብ መጋለጣቸው ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2011)በጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት ሳቢያ ከሦስት ሺህ በላይ ሰዎች ለከፋ ረሀብ መጋለጣቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። በምትክ መልክ የተሰጣቸው የእርሻ መሬትም ከመኖሪያቸው 60 ኪሎ ሜትር በመራቁ በእጅጉ መቸገራቸውን አስታወቀዋል። በጣና በለሰ ይሰራሉ የተባሉት ስኳር ፋብሪካዎችም እስካሁን ባለመጠናቀቃቸው ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸው መገለጹ ይታወሳል። በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ በጣና በለስ ተፋሰስ ወስጥ ከስምንት ዓመታት በፊት አካባቢው ለስኳር ልማት በመፈለጉና ከልማቱ ተጠቃሚዎች  ...

Read More »

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ አሸነፉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2011)በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በተካሄደ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ። የምርጫ ኮሚሽኑ ውጤቱን ይፋ ከማድረጉ በፊት የሃገሪቱ መንግስት በርዕሰ መዲናዋ ኪንሻሳ አድማ በታኝ ፖሊሶችሽን ያሰማራ ሲሆን ውጤቱም የተገለጸው ከለሊቱ 9 ሰአት እንደነበርም ተመልክቷል። ውጤቱ መገለጹን ተከትሎ የሚከተለውን አለመረጋጋት ለመግታት ሰው ከእንቅልፉ ሳይነቃ ውጤቱን መግለጽ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም ከምርጫ ኮሚሽኑ መረዳት ተችሏል። በአሁኑ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ ...

Read More »

የመጀመሪያው የአፍሪካ ንግድና የፋይናንስ አለም አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2011)አዲስ አበባ የአፍሪካ ንግድና የፋይናንስ አለም አቀፍ ጉባኤን ለመጀመሪያ ጊዜ ልታስተናግድ መሆኑ ተሰማ። የመጀመሪያ ነው የተባለውን አለም አቀፍ የአፍሪካ ንግድና ፋይናንስ አለም አቀፍ ጉባኤን የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋና ከሚገኘው Rescue shipping and investment Agency ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው መሆኑም ታውቋል። በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን የሚወክሉ የመንግስት መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት፤የፖሊሲ አውጪዎች፤የትልልቅ ኩባንያዎች ባለቤቶችና ...

Read More »

በብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና በግብረ አበሮቻቸው ላይ ክስ ተመሰረተ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2011) በብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና በግብረአበርነት በተያዙት የሜቴክ የስራ ሃላፊዎች ላይ ዛሬ በይፋ ክስ መመስረቱ ተሰማ። በተለያዩ ሰባት የሙስና ወንጀሎች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁንዲ፣ረመዳን ሙሳ፣ኮለኔል ደሴ ዘለቀ፣ቸርነት ዳናን ጨምሮ 8 ሰዎች መሆናቸው ተመልክቷል።

Read More »

ወለጋ ላይ ጦርነት አዲስ አበባ ላይ ሰላማዊ ትግል የሚለው አካሄድ ተቀባይነት የለውም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2011)ወለጋ ላይ ጦርነት አዲስ አበባ ላይ ሰላማዊ ትግል የሚለው አካሄድ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ሲል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓ አስታወቀ። የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ዓለሙ ስሜ ለኢሳት እንደገለጹት በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ በወለጋ ውጊያ እያደረገ በአዲስ አበባ ስለ ሰላማዊ ትግል መናገር አይቻልም ብለዋል። ሸኔ ኦነግ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በሶስተኛ ወገን እንደራደር ማለቱን በተመለከተ የፓርቲያቸውን አቋም ...

Read More »

በምዕራብ ጎንደር ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉበት ግጭት እየተመረመረ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2011)በምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉበትን ግጭት እየመረመረው መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ። የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ለኢሳት እንደገለጹት በመከላከያ ሰራዊቱ የተወሰደውን ርምጃ በተመለከተ የክልሉ መንግስት ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት አካል ጋር እየተነጋገረ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች ዛሬ መቀጠላቸውን ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ገልጸዋል። በሌላ በኩል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው አጭር ...

Read More »

የሞዛምቢክ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተከሰሱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 01/2011)በሞዛምቢክ በብድር የተገኘ የሃገር ሃብትን ያጭበረበሩ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተከሰሱ። የሃገሪቱ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትርን ጨምሮ በአጠቃላይ 18 ያህል ሰዎች በብድር በተገኘ 2 ቢሊዮን ዶላር ላይ የማጭበርበር ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው ሲከሰሱ ሁለት ዓለም አቀፍ ባንኮችም ተባባሪ ሆነው መገኘታቸውም ተመልክቷል። የሞዛምቢክ መንግስት በባለስልጣናቱ ላይ የማጭበርበር ወንጀል ክስ የመሰረተው የክሬዲት ስዊዝ ባንክ የቀድሞ ሶስት ሰራተኞች ለንደን ላይ በወንጀሉ ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተከትሎ ነው። ...

Read More »

ለውጡን ለማደናቀፍ በሚሰሩ አመራሮች ተቋማቸው እየተሽመደመደ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር1/2011)ለውጡን ለማደናቀፍ በሚሰሩ አመራሮች ተቋማቸው እየተሽመደመደ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሰራተኞች አመለከቱ። በደል እየደረሰብን ነው ያሉ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሰራተኞች ለኢሳት በላኩት መግለጫ እንዳሉት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተመራው ለውጥ የተቋሙን ዋናና ምክትል ስራ አስኪያጆች እስከማባረር ቢያበቃም በድርጅቱ ውስጥ ተሰግስገው ያሉ ግብረአበሮቻቸው አሁንም ችግር እየፈጠሩ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባለፉት አስርት አመታት አዲስ ዘመን ጋዜጣን፥ ኢትዮጵያ ሄራልድን ቀጥሎም አልአለምንና ...

Read More »